የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የተቋቋመው የድጋፍ አድራጊ ኮሚቴ ወደ ስራ መግባቱን አሳወቀ

0
81
በትላንትናው እለት የተቋቋመው የአስተዳደሩ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሱልጣን አልዪ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት በአለም የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በሚሰሩ ስራዎች ዜጎች እንዳይጎዱ ሁሉም ዜጋ ከአስተዳደሩ ጎን በመሆን የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሰብሳቢው ከዚህ ጋር በማያያዝ በአስተዳደሩ በጎ አድራጊዎች በገንዘብ ድጋፍ ለሚያደርጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው 1000327404494 የባንክ ቁጥር እንዲሁም የአይነት ድጋፍ የሚያደርጉ በአስተዳደሩ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
ወጣቱ በራሳቸው ተነሳሽነት እያደረጉት ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲሄድ ሁሉም ዜጋ ለዚህ በጎ ተግባር ያለበትን ሀላፊነት በመወጣትና ያለውን በማካፈል የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ የድጋፍ አስተባባሪው ሰብሳቢ ጥሪ አቅርበዋል፡፡