በድሬዳዋ አስተዳደር በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ግለሰብ መገኘቱን ጤና ቢሮ አስታውቃል፡፡

0
164
ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉትን የቤተሰብ አባላትን ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን እና ውጤታቸው ለምርመራ መላንኩን ቢሮው በመግለጫው አስታውቃል ፡፡
በድሬዳዳዋ አስተዳደር ከአውስታራሊያ በመጣ አንድ የ42 አመት ጎልማሳ ላይ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች መታየታቸውን መነሻ በማድረግ በተደረገ ምርመራ በቫይረሱ መያዙን መረጋገጡ እ ና ወደ ለይቶ ማቆያ መወሰዱን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታውቃል፡፡
የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ፉአድ ከድር በሰጡት መግለጫ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው የታማሚው ባለቤትም ወደ ለይቶ ማቆያ ተወስደዋል፡፡
ደመቸውም ለምርመራ መላኩም ተጠቁዋል ከዚህም ባሻገር ታማሚው ህክምና ክትትል ያደረገባቸው ሁለት ክሊኒኮች ባለሞያዎች እና ከአየር መንገድ የተቀበለው ወንድሙን እና የወንድምየው ባለቤት ክትትል እየተደረገላቸው እንዳለ አስታውቀዋል፡፡
ግለሰቡ ምልክቱን እንዳሳየ እራሱን ያገለለ እና ምልክቶቹ ሲታዩበት ፈጥኖ ለጤና ቢሮ ያስተወቀ እንደነበር ጠቁመዋል፤ ሌላው ማህበረሰብም መሰል የህመም ስሜቶችን ሲመለከት ፈጥኖ በ6407 ነጻ የመረጃ ስልክ መስመር በመደወል እራሱን እና ማህበረሰቡን ከበሽታው እንዲታደግ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በዚህም ከበሽታው እራሱን መጠበቅ እንጂ ሊደናገጥ አይገባም ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋ፡፡
ለበሽታው ቁጥጥር እና ክትትል የሚያግዙ ቁሳቁሶችን እና ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም ለለይ ማቆያ የሚያግዝ ቤት በመደገፍ ማህበረሰቡ እእ ባለሃቱ ከጤና ቢሮ ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡