በድሬደዋ የኮሮና ቫይረስ አለመከሰቱ ተገለጸ

0
147
ድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአስተዳደሩ የኮሮና ቫይረስ አለመከሰቱን ገልጸዋል
ቀደም ሲል ከጅቡቲ ተመላሽ ዜጎችን በጉምሩክ ህንጻ ማስፈሩን በአስተዳደሩ ከንቲባ እንደተገለጸ ይታወሳል ሌሎች የቀሩ ዜጎችን በመጨመር በአጠቃላይ 1475 ከጅቡቲ ተመላሾችን በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ማስፈራቸውን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፉአድ ከድር ገልፀዋል ፡፡
ተመላሾች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጹት ኃላፊው የህመም ምልክት የታየበት ሰው አለመኖሩንም በመግለፅ ፡፡
በቀጣይም የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚቆዩና የ 14 ቀን የቆይታ ጊዜያቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ መጡበት ክልል የመመለሱ ተግባር እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡