ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መመሪያዎች መተግበር ላይ ብዙ ይቀረናል ተባለ፡፡

0
92
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚተላለፉ መመሪያዎችን በመተግበር ገና ብዙ እንደሚቀር የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አህመድ መሐመድ ቡህ ገለፁ፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ በትላንትናው እለት ተወያይተዋል በውይይቱም የሀይማኖት ተቋማት፣ ትራንስፖርት ቦታዎች እንዲሁም በገበያ መአከላት ማህበረሰቡ ያለውን ግንኙነት በሀገራችን ምንም አይነት ወረርሽኝ የተፈጠረ አይመስልም ማህበረሰቡ ይህ ችግር በአስተዳደሩ ቢከሰት ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ ሊያስከትል በመቻሉ የሚተላለፍ መልዕክቶችን በመተግበር ሊከላከል እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር እንደተናገሩት በመጋዘን የታሸጉ ምግቦች እና የዋጋ ጭማሪ አድርገው የሚሸጡ የንግድ ድርጅቶችን ለፀጥታ ኃይሉ በመጠቆም ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡