ከኢትዮ ጅቡቲ የድንበር ወሰን የተመለሱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አህመድ ቡህ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

0
85
ከንቲባ አህመድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መጋቢት 17 /2012 ዓ.ም 814 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ከኢትዮ ጅቡቲ የድንበር ወሰን የተመለሱ ዜጎችን ድሬዳዋ መግቢያ ጫፍ 5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ ህንፃ ውስጥ ለ 14 ቀናት አስፈላጊው ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገላቸው በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
ተመላሾች በሚኖራቸው ቆይታ ለበሽታው ተጋላጭ እንዳይሆኑ በየሁለት ሜትር ርቀት እንዲቆዩ መደረጉን በመግለፅ የምግብ፣ የመጠጥ፣ አልባሳት፣ የንጽህና መጠበቂያ፣የጤናና የፀጥታ እንዲሁም የደህንነት አገልግሎት በሙሉ በአስተዳደሩ ወጪ የሚሸፈን መሆኑን ከንቲባ አህመድ ገልፀዋል፡፡
ተመላሾች 14 ቀናት በኋላ አስፈላጊው የመለየት እና የማጣራት ምርመራ ሂደት በኋላ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ዝግጅት በማድረግ ወደ መጡበት ክልል እና የትውልድ ቦታቸው እንዲሸኙ እንደሚደረግም ገልፀዋል፡፡