በድሬደዋ የሚገኘው ሸሙ ፋብሪካ በአስተዳደሩ የኮሮና በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እሚያግዙ 200 ካርቶን ደረቅና 200 ፍሬ ባለ 5 ሊትር ፈሳሽ የንጽህና መጠበቂያ ሳሙና ድጋፍ አደረገ፡፡

0
83
ፋብሪካው ያረገው ድጋፍ ለሌሎችም አርያ ሚሆን ተግባር ነው ተብሎዋል፡፡
የኮሮና በሽታ እንደ አለም ከፍተኛ ስጋት እየሆነ ባለበት በዚህ ወቅት በሀገራችን በሽታው ተስፋፍቶ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያስከትል ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በሽታውን ለመከላከል ለሁሉም ማህበረሰብ የቀረበውን ጥሪ መነሻ በማድረግም ሸሙ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በድሬደዋ አስተዳደር በሽታውን አስቀድሞ ለመከላ የሚያግዙ 200 ካርቶን ደረቅና 200 ፍሬባለ 5 ሊትር ፈሳሽ ንጸህና መጠበቂያ ሳሙና ድጋፍ አድርጉዋል፡፡
በድጋፉ ወቅት የፋብሪካው ኃላፊ አቶ ተስፋሚካኤል ጉኡሽ እንደተናገሩት እንደህዝብ ልንደጋገፍ የሚገባበት ወቅት አሁን ነው ያሉ ሲሆን በዚህም ፋብሪካችን በቀጣይም ከመንግስት የሚቀርብለትን ጥሪ ፈጣን ምላሽ ይሰጣል ሌላውም ባለኃብት ሊደግፍ ይገባል ብለዋል፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፉአድ ከድር በበኩላቸው ቢሮው በሽታወን አስቀድሞ ለመከላከል እያደረገ ላለው ጥረት መሰል ድጋፎች ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመው ሸሙ ፋብሪካም ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
በግለሰብ ደረጃም ዶ/ር ፈቲ መሀመድ የተባሉ ግለሰብ ግምቱ 40ሺብር የሚሆን የሰውነት ሙቀት መመርመሪያ ኪት ሰተዋል ይህም በቀጣይም ይጠናከር ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡