የድሬዳዋ የስፖርት ስመ ገናናነት በታዳጊዎች ይመለሳል ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር አፈ ጉባኤ የድሬዳዋ ፍቅርና ሰላሟ ና የቀድሞ የስፖርት ስመ ገናናነቷ በታዳጊዎቾ ይመለሳል ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናገሩ፡፡

0
97
የ2012 የድሬዳዋ አስተዳደር የትምህርት ቤቶች የስፖርት ፌሲቲቫልን በይፋ ያስጀመሩት ወ/ሮ ፈጡም ስፖርት የአንድነት ፣ የፍቅርና የመቻቻል መገለጫ በመሆኑ ታዳጊዎች የስፖርት መድረኮችን ዓላማ በመገንዘብ ከስፖርቱ በአግባቡ ተጠቃሚ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
የድሬዳዋ የስፖርት እድገት ምንጭ ት/ቤቶች መሆናቸውን የገለጹት አፈ ጉባኤ ፈጡም ሙስጠፋ ስፖርት ከውድድር ባለፈ በስነ ምግባር የታነጸ አገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችል በመሆኑ በትምህርት ቤቶች የሰውነት ማጎልመሻ መምህራን ከ40 ደቂቃ ትምህርት በዘለለ ታዳጊዎችን ለስነምግባር ትኩረት እንዲሰጡ ትኩረት በመስጠት መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
በድሬደዋ በርካታ ስፖርተኞች በስነ-ምግባር ችግር መድረስ ከሚገባቸው ትልቅ ደረጃ መድረስ ሳይችሉ ሲቀሩ ይስተዋላል ያሉት ወ/ሮ ፈጡም በቀጣይ ይህ የስነ ምግባር ችግር የስፖርት መሰናክል እንዳይሆን መምህራት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የ2012 ዓ.ም የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የስፖረውት ውድድር በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ብቃት ያላቸው ምርጥ ታዳጊ ስፖርተኞችን ብቃታቸውን የሚያሳዩበት ማራኪ ስፖርታዊ ትዕይነት የሚታይበት አዝናኝ የውድድር መድረክ ይሆናል ተብሏል፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ በእንግድነት ተገኝተው ለታዳሚው ባስተላለፉት መልዕክት የአስተዳደሩ ስፖርት ለማሳደግ ትምህርት ቤቶች ላይ የስፖርት እንቅስቃሴ እንዲጠናከር እንዲህ አይነት ውድድሮች ትኩረት ተሰጥቶ መደረጋቸው እንደሚያጠናክር ገለፀዋል ፡፡
የካቲት 28/6/2012 የተጀመረው የትምህርት ቤቶች ውድድር 24 ትምህርት ቤቶች ለቀጣይ 20ቀናት በተለያዩ ስፖርት ዓይነቶች ውድድራቸውን እንደሚያካሄዱታውቋል፡፡