የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ ነው

0
98
የኮሮና ቫይረስ እስካሁን በድሬደዋ ባይከሰትም አስተዳደሩ ቫይረሱን ለመከላከል የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ተገለፀ።
የዓለም የጤና ስጋት እና ወረርሽኝ የሆነው የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ በ6 ሰዎች ላይ ተገኝቷል።የቫይረሱን ወደ ኢትዮጵያ መግባት ተከትሎ እንደ ሀገር የስርጭት መጠኑን ለመቀነስ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑ ይታወቃል።
ይህን ተከትሎም የድሬደዋ አስተዳደር የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በአየር እና በየብስ የሚገቡ መንገደኞችን ሙቀት የመለካት ስራ እያከናወነ መሆኑንና፥ የለይቶ ማከሚያ ማዕከል ማዘጋጀቱን እንዲሁም በተለያዩ ቦታዋች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ገልጸዋል።