የእጅ ንፅህና መጠበቂያና የመተንፈሻ አካልን መሸፈኛዋች ያለአግባብ ዋጋ ጨምሮ ሲሸጥ የነበረ አንድ የመዳኒት ድርጅት ታሸገ።

0
90
የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብአትን ጥራት ቁጥጥር ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ሲ/ር ሳሬዶ ለጋዜጠኞች በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል የህክምና መገልገያ ያለአግባብ ዋጋ ጨምረው የሚሸጡ የመዳኒት ድርጅቶችን ለመከታተል በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ሰብሳቢነት ከተለያዪ ተቋማት ግብረ ሀይል መቋቋሙን ገልጸዋል።
በዚህም ከኮሮና ቫይረስ በሀገራችን መከሰት ጋር ተያይዞ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ የንግድ ተቋማት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንና ህብረተሰቡ የዋጋ ጭማሪ የሚያረጉ ድርጅቶችን በጤና ቢሮ በመምጣት ጥቆማ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል ፡፡
ጥቆማ ለመስጠት በነዚህ ስልክ ቁጥሮች መጠቀም ይችላሉ
0251111394
0251112330