የአስተዳደሩ ፖሊስ አባላት ለታላቁ ለህዳሴ ግድባችን አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታወቁ ::

0
102
የድሬዳዋ አስተዳደር የፖሊስ ኮሚሽን ሰራተኞች እና አባላት ለታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የአንድ ወር ደሞዛቸው በአንድ አመት ከፍለዉ ለማጠናቀቅ ቃል ገብተዋል ፡፡
በአንድ አመት ዉስጥ ከተቋሙ በ6 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዢ ለመፈፀም መስማማታቸዉን ዛሬ ጠዋትየድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና የለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ግምቹ ካቻ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ ገልፀዋል ፡፡
ኮማንደር ገመቹ ካቻ አክለዉም በቀጣይም ፖሊስ ኮሚሽኑ ከሚያበረክተው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ አስፈላጊ በሆኑ ግዳጆች ሁሉ ላይ በመሰማራት ለህዳሴ ግድብ ድህነት ለመጠበቅ እስከ ህወት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸዉን የፖሊስ አባላት ተናግረዋል ብሏል ፡፡