ከየካቲት 18/2012 ዓ.ም ጀምሮ በሐረር ከተማ ሲሰጥ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ እና የሐረር መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቋል::

0
23
በስልጠናው መዝጊያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ አህመድ ቡህ ሰልጣኞቹን “በቀጣይ ወደ ስራችሁ ስትመለሱ በአገልጋይነት መንፈስ ስራችሁን እና ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ” ሲሉ አሳስበዋል::
በመደመር ጎዳና በመጏዝ መዳረሻችንን ብልፅግና እናደርጋለን ብለዋል ከንቲባው በንግግራቸው::
580 የሚሆኑት እና ስልጠናቸውን ያጠናቀቁት መካከለኛ አመራሮቹ በሐረሪ ክልል አፈጉባኤ ወ/ሮ ሚስራ አብደላ አስተባባሪነት 44,500 ብር ከኪሳቸው በማሰባሰብ ለበጎ አድራጎት ለግሰዋል::
የድሬዳዋ እና የሐረሪ ክልል የብልፅግና ፓርቲ መካከለኛ አመራሮች በሐረር የተሰጣቸው ስልጠና መዝጊያ መድረክ ላይ የሐረሪ ክልል ር/መስተዳደር ኦርዲን በድሪ ለተለያዩ አካላቶች የምስጋና የማስታወሻ ስጦታ አበርክተዋል::