በድሬደዋ የኮረና ቫይረስ ስጋትን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

0
35
አለም አቀፍ ስጋት የሆነውን የኮረና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የሚያስችለውን የቅድመ ክትትልና ቁጥጥር ስራ እየሰራ እንዳለ የድሬደዋ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ቢሮው
የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኮረና እንደ ድሬደዋ አስተዳደር እስካሁን ባይከሰትም ምልክቱ እንደ ሀገር መከሰቱን ተከትሎ በድሬደዋ አስተዳደርም የመግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ ቀጥሉዋል ብለዋል ፡፡
የቢረሮ ምክትል ሀላፊ አክለውም የለይቶ ማቆያ ቦታን ማዘጋጀት የጤና ባለሙያውም ሆነ ማህበረሰቡ ማስገንዘብና በቂ ግብአት የማዘጋጀት ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
ማህበረሰቡም ከመደናገጥ ተቆጥቦ በሽታው ምልክት ሲያይ ፈጥኖ ለቢሮው እንዲያሳውቅና ታማሚውን ወደ ጤና ተቋም እንዲሁድ የማድረጉ ስራ እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል፡፡