በሐረር ከተማ ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙት የብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ እና ሐረሪ ክልል መካከለኛ አመራሮች ደም ለግሰዋል::

0
55
በደም ልገሳው ላይ የስልጠናው አወያይ እና አስተባባሪ ከፍተኛ አመራሮችም ተሳታፊ ነበሩ:: ሐረር እየወሰዱ ከሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና ጎን ለጎን የሐረር ከተማ የተለያዩ ቦታዎችን በአንድነት አፅድተዋል በእረፍት ቀናቸው ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ተግባር ሰርተዋል ::
የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የሐረሪ ክልል ር/መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የድሬዳዋ እና ሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ከስልጠናው ጎን ለጎን በተተገበሩ ተግባርት ላይ ተገኝተዋል
የብልፅግና ፓርቲ መካከለኛ አመራሮች ሐረር እየወሰዱት በሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ በእረፍት ቀናቸው በሐረር ከተማ 4 ቦታዎች የሚገኙ ታሪካዊ ሙዚየሞችን ጎብኝተዋል::
በስልጠናው መድረክ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት የሶማሊ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፋ መሀመድ እና የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተገኝተዋል::
ርዕሰ መስተዳድሮቹ በመድረኩ ተገኝተው የስልጠናውን ሂደት የተመለከቱ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት ሰልጣኞቹ ለነበራቸው ንቁ ተሳትፎ አመስግነው በቀጣይ ከብልፅግና ጋር ለሚኖራቸው ጉዞ ስኬታማነት ሊከተሏቸው የሚገቡ መርሆች ላይ የማነቃቂያ ንግግር አድርገዋል::