ሴቶች ያላቸውን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ለውጡን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ይገባቸዋል ተባለ

0
28
በአስተዳደራችን መንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያሉ ሴት የቡድን መሪዎችን ወደ ውሳኔ ሰጪነት ለማምጣትና የሀገራችንን ለውጥ ለማስቀጠል እንዲያግዝ በማሰብ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአመራር ሰጪነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በአስተዳደሩ ካይዘን ኢንስቲቲዩት አማካኝነት የሴቶች የአመራር ሰጪነት ላይ በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሳተፉ ሴቶች እንደተናገሩት የሀገራችን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እንደ ሀገር በፌደራል ደረጃ ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት ያደረጉት ተግባር ወደ ክልሎች በማውረድ ሴቶች ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው ሀገራችን የያዘቸውን ለውጥ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የበኩላቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
በስልጠናው የተሳተፉ ተሳታፊዎችቸም አክለው እንደገለጹት ሴቶች በፖለቲካው ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎታቸው ዝቅተኛ መሆን ፣ ወደ አመራርነት ለመምጣት የሚደረገው ጥረት ዝቅተኛ መሆን እና በብቃቷ ያመጣችው ነው ብሎ አለማሰብ እንዲሁም የኢኮኖሚ ጥገኛ መሆኗ ዋነኛ የሚስተዋሉ ችግሮች በመሆናቸው በቀጣይ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ሴቶች ተደራጅተው በመወያየትና በመነጋገር መፍትሔ ለመፈለግም የመንግስት ሰራተኛ ማህበር ለማደራጀት ተወያይተዋል፡፡
ስልጠናውን ያሰለጠነችው ወ/ሪት ሱአድ መሀመድ እንደተናገረችው ስልጠናው ሴቶች ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው በተቋማቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡
አሰልጣኝ ሱአድ አክላም ሴቶች በባህል፣ በኢኮኖሚና በአመለካከት ያሉብንን ችግሮች ተቋቁመን በተፈጥሮ ያለንን ጸጋ አክለው ከዚህ በተሻለ በመንቀሳቀስ እንደ ሀገር የተጀመረው ለውጥ ላይ በመሳተፍ የድርሻቸውን እንዲወጡም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡