ለድሬዳዋ እና ለሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡

0
26
ዛሬ በተጀመረው ስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ሃገራዊ የለውጥ እርምጃዎች፣ ርዕዮት ዓለምና እንድምታዎቹ፣ የፓለቲካ ብልፅግናን የማረጋገጥ ትልም እና ፈተናዎቹ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ትልም እና ፈተናዎቹ የስልጠናው የትኩረት ነጥቦች ናቸው ብለዋል::
መካከለኛ አመራሮቹ በስልጠናው ሂደት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና ከስነ ምግባር ጋር የተያያዙ ችግሮች ሊኖሩ እንደማይገባም አቶ ኦርዲን አሳስበዋል::
ከድሬዳዋ እና ከሐረሪ ክልል ለተውጣጡ 580 የብልፅግና ፓርቲ መካከለኛ አመራሮች መሰጠት በተጀመረው ስልጠና መክፈቻ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጀማል በከርን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ እና ሌሎች ኃላፊዎች ተገኝተዋል::
ለ11 ቀናት በሚቆየው የመካከለኛ አመራሮቹ ስልጠና ሀገራዊ የለውጥ እርምጃዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ቀርቦ ሰልጣኞቹ በ12 ቡድኖች በመከፋፈል ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል::