የኢትዮጵያ ኦ/ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ አቡነ ማትያስ በድሬዳዋ ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመሰጠቱ ለአስተዳደሩ ምስጋና አቀረቡ።

0
63

በድሬዳዋ መሐል ከዚራ በሚገኘው ሚካኤል ቤተከርስቲያን በተዘጋጀው የምስጋና መርሀግብር ላይ የተገኙት ብፁእ አቡነ ማትያስ አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኗን የዘመናት ጥያቄ ተቀብሎ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመስጠቱ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ቤተከርስቲያኗ ለምትሰጠው አገልግሎት ድጋፍና ትብብር ላበረከቱ ተቋማትም የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።

በምስጋና መርሀግብሩ ላይ የተገኙት ከንቲባ አህመድ ቡህ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ በቅርስነት በመመዝገቡ የተሰማቸውን ደስታ ለብፁእ አቡነ ማትያስ የገለፁ ሲሆን በአሉ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር አስተዳደሩ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፀዋል። የፊታችን እሁድ በታላቅ ድምቀት በሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ ላይ እና በምስጋና መርሀግብሩ ላይ ለመገኘት ወደ ድሬዳዋ የመጡት ብፁእ አቡነ ማትያስን ከንቲባ አህመድ ቡህ እና ም/ከንቲባ ከድር ጁሀር በድሬዳዋ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአስተዳደሩ የመንግስትና የድርጅት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችን ጨምሮ በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምእመናንም በምስጋና መርሀግብሩ ላይ ታድመዋል ። ታህሳስ 14 ቀን 2012 ዓ.ም አስተዳደሩ ለ82 የእምነት ተቋማት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል። ምንጭ የድሬደዋ አስተደደር ከንቲባ ጽ/ቤት