ትውልድ ተሸጋሪ አጀንዳዎችን እናስብ፤ እንተግብር

0
72

ይህች ዓለማችን በርካታ ሀሳቦች በተለያዩ የድምጽ ቃናዎች ታጅበው እዚህም እዚያም የሚደመጡባት ናት፡፡ ከእነዚህ አስተሳሰቦች መሀል በቁጣ ድምጽና በመሳሪያ ታጅበው ሳንፈልጋቸውና ሳናምንባቸው እንድንቀበላቸው የሚያስገድዱ ናቸው፡፡እነዚህ አስተሳሰቦች የዜጎችን መብቶች ለመጣስና ነጻነትንና ዴሞክራሲን ለማጥፋት እንደተነሱ ገና ከአነሳሳቸው የሚያስታወቁ ናቸው፡፡

ሌሎቹ አስተሳሰቦች ደግሞ በማባበያ ቃላትና በበሬ ወለደ የፈጠራ ወሬ የታጀቡ ሲሆን የዋሆችን የማሳመን አቅማቸው ግን ከፍተኛ ነው፡፡ ብዙዎችን ስሜታዊ በማድረግ የነገውን አርቀው እንዳያስተውሉና ትውልድ ተሸጋሪ አስተሳሰብ ውስጥ እንዳይገቡ እንቅፋት ይሆናሉ፡፡ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ነውና ብሂሉ ዜጎች በስሜታዊነት ተነሳስተው ጠብና ሁከት እንዲፈጠር፤ በዚህም ሀገር እንዳትረጋጋና ወደ ሠላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ  እንዳትገባ ተግዳሮት ሆነው ቆይተዋል፡፡

ሌላውና ከላይ ከጠቀስናቸው አስተሳሰቦች ለየት የሚለው ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበና አሁን ካለው ተጨባጭ እውነታ በመነሳት በብዙዎች ሊታመንብት የሚገባ ራዕይን የሚያመላክት ነው፡፡ እንዲህ ያለውን አስተሳሰብ በርካቶች ሳይገደዱና ሳይታለሉ በጋራ ለመልማትና ነገን የተሸለ ለማድረግ ካላቸው ተመሳሳይ ፍላጎት በመነሳት በዙሪያው የሚሰለፉለት አስተሳሰብ ነው፡፡

እነዚህ አስተሳሰቦች በየዘመኑ የነበሩና ለወደፊትም በህዝብ መሀል ተደብቀው የሚኖሩ ሲሆን ዕድሉን ሲያገኙና ወደ ሥርዓትነት ሲቀየሩ ለሀገር ልማትም ሆነ ውድመት መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው፡፡ ለሀገር ልማት ጠንካራ መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ አስተሳሰቦች ወደ ሥርዓትነት እንዲቀየሩ እና ለሀገር ውድመት መነሻ የሚሆኑትን አስተሳሰቦች ደግሞ ወደ ሥርዓትንት እንዳይቀየሩ ትልቁንና የአንበሳውን ድርሻ መወጣት ያለበት ህዝብ ነው፡፡ ምክኒያቱም እነዚህ ሁሉም አስተሳሰቦች ከህዝብ ውጪ ከባህር እንደ ወጣ ዓሣ ህልውና ስለማይኖራቸው ነው፡፡

ሠነፎች ትውልድ ተሻጋሪ ሥራ ከመሥራት ይልቅ ቁጭ ብለው ሀገር የሚያፈርስ እና ትውልድን የማይገነባ  አሉባልታቸውን ይፈበርካሉ፡፡ ደካሞች ደግሞ ችግሮችን እየፈለፈሉ የሚሠራውን ከማብጠልጠል ያለፈ አንዳች የሚረባ መፍትሄ በአማራጭነት ሳያቀርቡ አና የመፍትሄ አካል ከመሆን ይልቅ የችግር አካል በመሆን የትውልድን ልብ ያዝላሉ፡፡

ብርቱዎች ግን ለማንኛውም ችግር አማራጭ የሚሆን የመፍትሄ ሀሳብ ከማቅረብ በዘለለ የመፍትሄው አካል በመሆን ትውልድን የሚሻገር ሥራ ይሠራሉ፡፡ እንግዲህ መደመራችን ላልቀረ ወደዚህኛው አስተሳብና ተግባር እንደመር፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

                                                     ድሬዳዋ

                                                       09/02/2011ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here