በዘንድሮ የክረምት በጎፍቃድ ስራ የወጣቶች ተሳትፎና ተነሳሽነት ጨምሯል

0
236

በ2011 ዓ.ም የክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት የወጣቶች ተሳትፎና ተነሳሽነት መጨመሩ ተገለፀ፡፡
በክረምት የዕረፍት ወቅት የተለያዩ የበጎፍቃድ አገልግሎቶችን ለመስጠት የህብረተሰቡን ማህበራዊ፣
ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ለመቀነስ ዓላማን አንግቦ እየተካሄደ ባለው የ2011 ዓ.ም
የክረምት የበጎፍቃድ አገልግሎት በተለይ በትምህርት እና ስልጠና በጎፍቃድ ስራ የወጣቶች ተሳትፎና
ተነሳሽነት መጨመሩ ታውቋል፡፡

እንደ አስተዳደር በርካታ ወጣቶች እየተሳተፉበት ያለው የክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት ከተለያዩ
የበጎፍቃድ ስራዎች እየተከናወነ ሲሆን በተለይ ለ05 ቀበሌ በትምህርት ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባሻገር
12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች ሳይቀሩ በበጎ አድራጎት ስራው እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል፡፡
በ05 ቀበሌ የስፖርት ባለሞያ ወ/ሮ ምህረት እንደተናገሩት 552 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበጎ
ፍቃድ አገልግሎቱ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን ከወትሮ በተለየ መልኩ 52 የ12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች
በበጎፍቃድ ተመዝግበው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቀበሌው የአረጋዊያን ቤት ጥገና፣ የምግብ ድጋፍ፣ የተማሪዎች የኮምፒውተር ስልጠና፣ የችግኝ
ተከላ እና እንክብካቤ፣ የደም ልገሳ፣ የትምህርትና ስልጠና የበጎ አድርጎት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን
በአረጋዊያን ቤት ጥገና ረገድ ድጋፍ እያፈላለጉ መሆኑን እና በትምህርት ዘርፍ በቂ የቁሳቁስ ድጋፍ
አለመኖሩን እንደችግር አንስተዋል፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ግን የወጣቶች ተሳትፎና ተነሳሽነት
አበረታች የሚባል መሆኑ ተገልጿል፡፡