በኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 353 ሚሊዮን 633 ሺህ ችግኝ ተተከለ

0
164

እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 353 ሚሊዮን 633 ሺህ 660 ችግኝ በዛሬው እለት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ  ተተክሏል፡፡

 

በአገር አቀፍ ሚዲያዎች የአረንጓዴ አሻራ ቀን አስተባባሪ ኮሚቴ በሰጡት መግለጫ እንደ ሀገር በእለቱ ከእቅድ በላይ መከናወኑን አስታውቀዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ የተቀመጠውን የአረንጓዴ አሻራ ቀን እውን ለማድረግ በድሬደዋ

በችግኝ ተከላው መርሀ ግብር የአስተዳደሩ ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ ፣ የአስተዳደሩ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች በተዘጋጁ 6 ቦታዎች ችግኝ ተክለዋል፡፡

በእለቱ 2መቶ ሺህ ችግኞች ለመትከል እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በህብረተሰቡ ተሳተፎና በተደረገው ዝግጅት 256 ሺህ በላይ ችግኝ መትከል ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ህንድ 66 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር በመትከል ክብረ ወሰኑን ይዛ የቆየች ሲሆን ይህ ክብረወሰን በትላንትናው እለት የአረንጓዴ አሻራ ቀን ተሻሽሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here