የአረንጓዴ አሻራ በድሬደዋ ተጀመረ ፡፡

0
379

እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 200 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ በድሬዳዋ ነዋሪዎች በአንድ ጀንበር 200 ሺህ ችግኝ የመትከል ሂደቱ ተጀምሯል። በድሬደዋ አስተዳደር ከተዘጋጁት 6 መአከላት አንዱ በሆነው መከላከያ ሪፈራል ሆስፒታል የመከላከያ ሰራዊትና የፅጥታ አካላት የችግኝ ተከላ እያካሄዱ ይገኛሉ። የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ሂደት ከንጋት አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እየተካሂደ ነው ፡፡በአስተዳደሩ ከሐምሌ 22/2011 እስከ ነሐሴ 22/2011 በጥቅሉ 871 ሺህ ችግኝ ለመትከል ከተያዘው እቅድ ውስጥ በአንድ ጀንበር 200 ሺህ ችግኞችን ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም. በ6 መአከላት የመትከሉ ሂደት ተጀምሯል ።

የዚህ የአረንጓዴ አሻራ በማኖር ሂደት ከንጋት አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12 ሰአት ድረስ 20 ሺህ ችግኞችን በመከላከያ ሪፈራል ሆስፒታል ይተከላሉ።

በቀጣይ በሪፈራል ሆስፒታሉ የተተከሉት ችግኞች በግለሰብ ደረጃ የመከላከያ ሰራዊት አባላት 10 ችግኞችን በመንከባከብ እንዲያፅድቁ አቅጣጫ እንደተቀመጠና የውሀ ማጠጫ ቧንቧ መስመር መዘርጋቱን  የምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል አዛዥ ኮኒኔል ሀጎስ ሀዱሽ ገልፀዋል።

   በሪፈራል ሆስፒታሉ በአትክልተኛነት እየሰሩ የሚገኙት አቶ ጀሩ ደሳለኝ በሰጡት አስተያየት የተተከሉ ችግኞችን አንደልጅ ተንከባክበው

ለማፅደቅ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

 በችግኝ ተከላው የተሳተፉ የመከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ አካላት በሰጡት አስተያየት በየግላቸው የደረሳቸውን 10 ችግኞች ተንከባክበው በማፅደቅ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here