የኦሎምፒክ ሳምንት የጎዳና የሩጫ ውድድር

0
336

የኦሎምፒዝም የሰፖርት መረሆዎችን አላማ ታሳቢ በማድረግ የሚከበረው የኦሎምፒክ ሳምንት በከተማችን ድሬደዋ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተከበሯል፡፡ ከነዚህ መርሀ ግብሮች መካከል የ5 ክሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ሳምንቱን አድምቆታል፡፡ ለወደፊት እሮጣለሁ በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ከህፃናት እስከ አዋቂዎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካፈለ ነበር፡፡

 

የአለም የኦሎምፒክ ሳምንት በዚህ ደማቅ የሩጫ ውድድር ጅማሮውን ያደረገ ሲሆን ስፖርት ለሰላም፣ ስፖርት ለአንድነት፣ ስፖርት ለሰውልጆች መከባበር እና መፋቀር፣ ስፖርት ለህዝብ ለህዝብ ትስስር እና የመሳሰሉ የኦሎምፒዝም መርሆዎች በሰፊው ተንፀባርቀውበታል፡፡

ውድድሩን በአካል በመገኘት እና በውድድሩ በመካፈል ያስጀመሩት የድሬደዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ክሚሽነር እና ኡመር የኦሎምፒዝም መሮዎች  የሆኑትን የሰላም፣ የአንድነት እና የሰው ልጆች የእርስ በእርስ ትስስር እና መከባበር እሴቶች በሚገባ ተጠቅመንባቸው የወደፊት ኢትዮጵያን በብሩህ ትውልድ የተሞላች ለማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በመሰል መልካም እሴቶች በመጠቀም ከጥላቻና ከዘረኝነት የነፃ ማህበረሰብ ማፍራት ይገባል ይህም በስፖርት እና በኦሎምፒዝም መርሆዎች ይቻላል ብለዋል፡፡  ውድድሩ መነሻና መድረሻውን ምድር ባቡር አደባባይ በማድረግ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here