የኦሎምፒክ ሳምንት በድሬዳዋ በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ እየተከበረ ነው

0
308

     ለአለም አቀፍ መድረኮች አገራችን ኢትዮጵያ ያስጠሩ እና ሰንደቅ አላማችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረጉ አትሌቶች አሉን፡፡

 

     እነዚህ አትሌቶች እና በአለም አቀፍ መድረክ ያለን ገናና ዝና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለኦሎምፒክ ስፖርት እና ለኦሎምፒዝም ትልቅ ትኩረት በመስጠት በአገር አቀፍ ደረጃ ንቅናቄ ይደረጋል፡፡

     በከተማችን ድሬዳዋም ኦሎምፒክ ሳምንት በከፍተኛ ህዝባዊ ተሳትፎ እና ንቅናቄ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

     ከድሬዳዋ ጀማል ሮጎራን፣ ሰለሞን ተሰማን በብስክሌት እንዲሁም ሻምበል የማነህ በቦክስ ስፖርት ኢትዮጵያን በመወከል በአለም አቀፍ መድረኮች በኦሎምፒክ መሳተፍ የቻሉ ስፖርተኞችን አፍርታለች፡፡

በቀጣይም ተተኪና ስመ ጥር አትሌቶችን በብዛት ለማፍራት የኦሎምፒክ ሳምንት የንቅናቄ ስራ ይሰራል፡፡

     የኦሎምፒክ መርሆ እና የመሳሰሉ ጠቃሚ የኦሎምፒዝም መርሆዎች ለከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎን ንቅናቄ በግንዛቤ ማስጨበጫ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

     የኦሎምፒክ ሳምንት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አና ኡመር የኦሎምፒክ ሳምንት መበሰሩ ስፖርቱን ህዝባዊ መሰረት ለማረጋገጥ ሰፊ የህብረተሰብ ንቅናቄ ከመፍጠር ባለፈ ስፖርት ለሰላም፣ ስፖርት ለአንድነት፣ ስፖርት ለመልካም ምግባር እና ስፖርት ለትብብር የሚሉ የኦሎምፒዝም መርሆችን ተግባራዊ ይደረጉበታል ብለዋል፡፡

     ሳምንቱ በጎዳና ሩጫ፣ በጽዳት ዘመቻ፣ በደም ልገሳ፣ በተለያዩ ስፖርታዊ ሁነቶች፣ በኪነ ጥበብ እና ኮንሰርቶች እንዲሁም በሲምፓዝየም እንደሚከበር አስታውቀዋል፡፡

     በዋናነት ግን የኦሎምፒዝም መርሆ የሆነውን ስፖርት ለእርስ በእርስ ትስስር፣ ስፖርት ለሰላም እና ለአንድነት እንዲሁም ስፖርት ለሰው ልጆች ሰባዊ ክብር የሚሉት መርሆች ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶቸው እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here