አመለ ሸጋው አሰግድ ተስፋዬ ታስቦ ውሏል

0
442

በእግር ኳስ ሂወቱ በርካቶችን ያስደመመው አሰግድ ተስፋዬ ( ፔሌ ) ሁለተኛ  ሙት ዓመት መታሰቢያ በእግር ኳስ ጨዋታ ዝግጅት ተከብሯል፡፡ የአሰግድ ተስፋዬ ሁለኛ ዓመት ታስቦ ሲውል በርካቶች አሁንም ድረስ ከአይምሮአቸው የማይጠፋውን የእግር ኳስ ችሎታውን በማስታወስ ነበር፡፡

አመለሸጋው አሰግድ ተስፋዬ ከእግር ኳስ ችሎታው በተጨማሪ በስፖርታዊ ጨዋነት ለበርካታ ተጫዋቾች አርያ መሆን የቻለ ነው፡፡ ዛሬም ድረስ ህልፈቱ ለበርካቶች አስደንጋጭ ቢሆንም ምርጡ ተጫዋች ላይመለስ ሄዷል፡፡ ነግር ግን እሱ ጥሏቸው የሄዳቸው አሻራዎች ዛሬም ድረስ ህያው ናቸው፡፡

አሰግድ ተስፋዬ ለታዳጊዎች መነቃቃት የፈጠረ ለተተኪዎችም ትልቅ ትኩረት ለመስጠት አካዳሚ እስከማስገንባት የደረሰ ተጫዋች ነበር፡፡ ለምርጡ ተጫዋች መታሰብያ በተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር  ላይ የጅግጅጋ፣ የሀዋሳ እና የድሬ ጤና ቡድኖች ተሳታፊ መሆን ችለዋል፡፡

ድሬ ጤና ቡድን ከድሬደዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ የመታሰቢያ ውድድር የኦሎምፒክ ሳምንት እግረ መንገዱን አድምቆት አልፏል፡፡ ለዚህ ውድድር ልዩ የተጫዋቹ የህይወት ታሪክ የቀረበ ሲሆን የህሊና ፀሎት ተደርጎለት ውድድሩ ተካሂዷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here