1440ኛው የኢድ -አልፈጥር የስግደት ስነ-ስርአት ተመላሾች የቁርስ ግብዣ ተደረገ

0
386

በድሬደዋ አስተዳደር ልዩ ስሙ መስቀለኛ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለ1440ኛው የኢድ-አልፈጥር የስግደት ስነ-ስርአት ተመላሾችን የቁርስ ግብዣ አደረጉ፡፡

 

በስነ-ስርአቱ ተሳታፊ የነበሩ የእምነቱ ተከታዮች በሰጡት አስተያየት ድሬዳዋ ቀድሞ የነበራት ፍቅር የተመለከቱበትና  በጋራ ደስታን የማሳለፍ ሂደት እና ድባብ እንዳጣጣሙት ተናግረዋል፡፡

አስተያየት ሰጪዎች አክለውም የድሬደዋ መገለጫን አዲሱ ትውልድ በልዩ ፍቅር ሊንከባከበው ይገባል፤ እኛም ፍቅራችንንና ህብረታችን በማጠናከር የተሸለች ድሬዳዋን ገንብተን ለአዲሱ ትውልድ የማስረከብ ሃላፊነታችን እንወጣለን ብለዋል፡፡

የቁርስ ስነ-ስርአቱ ድሬደዋን ፍቅር መሆኗን ያሳየና የህዝቡን አንድነት ያመላከተም ነበር፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here