1440ኛው ታላቁ የኢድ-አልፈጥ በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር በድምቀን ተከብሯል ፡፡

0
386

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በረመዳን ወር ያዳበርነውን የሰላምና የመረዳዳት ልምድ በማስቀጠል የሀገራችንን ሁለንተናዊ ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

 

በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ህዝበ ሙሰሊም ከማለዳው 12 ሰዓት አንስቶ ነበር የተለያዩ ሀይማኖታዊ ተግቢርታዎችን በማሰማት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኘው የኢድ-ሷሏት  መስገጃ ቦታ ያመሩት፡፡

በኢድ-ሷሏት መስገጃ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ መሀዲ ጊሬ እንዳሉት የኢድ-አልፈጥ በዓል ለዘመናት በቆየው ባህላችን መሰረት ከዘመድ፣ ከወዳጅ ከጎረቤት ጋር እንኳን አንደረሳቹ እየተባባልን ያለንን ዝምድናና ወዳጅነት የምናጠናክርበት በመሆኑ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በመጠቆም  በረመዳን ወር ያዳበርነውን የሰላም፣ የመረዳዳት ልምድ በማድረግና በማስቀጠል የሀገራችንን ሁለንተናዊ ሰላም በማረጋገጥ በዓሉ የሰላም የፍቅር የይቅርታና የአንድነት በአል እንዲሆንም አቶ መሀዲ ጊሬ የመልካም ምኞታቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡

 የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ኡስታዝ አዩብ ሀሰን በበኩላቸው ሙሰሊም አንድነቱን በመጠበቅ ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር በጋራ በመስራት እንዲሁም ከተማዋ ከዚህ ቀደም የምንተዋወቅበትን ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በመቻቻል በአንድት የመኖር ባህልን አሁንም ለማስቀጠል በጋራ መስራት እንደሚገባም ነው ኡስታዝ አዩብ ሀሰን የተናገሩት፡፡

 ህዝበ-ሙስሊሙ የኢድ-አልፈጥር በዓልን ሲያከብር ያለው ለሌለው በማካፈል የተቸገሩትን በመርዳት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ በኢድ-ሷሏት ስግደቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ ነዋሪዎች ተናግረው በረመዳን ፆም ወቅት የነበረውን የመረዳዳትና በጋራ አብሮ ነገሮችን የመፈፀም ሂደት በቀጣይም በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሚገባም በእለቱ ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here