‹‹የኢድ-አልፈጥር በዓል በጎ ተግባራትን በማድረግ እናክብር›› የሐይማኖት አባቶች

0
408

የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮና የብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ በጋራ በመሆን በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የኢድ-አልፈጥር የዋዜማ በዓል ስነ-ስርዓት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተከብሯል፡፡

 

በስነ ስርዓቱ የተሳተፉ የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት የኢድ-አልፈጥር በዓልን ስናከብር በጎ ተግባራትን በማድረግ እናክብር ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልዬ የአስተዳደሩን ምክትል ከንቲባ በመወከል ባስተላለፉት መልእክት ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ጾም በመንፈሳዊ ሕይወት ያካበታቸውን መልካም እሴቶች ለጋራ መግባባት፣ ለልማታችንና ለእድገት እንዲሁም አንድነታችንን ለማረጋገጥ እንዲያውለው ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ህዝበ ሙስሊሙ በተለይ ወጣቱ እስልምና የሰላም እምነት መሆኑን ተገንዝቦ በረመዳን ፆም ያዳበረውን ኃይማኖት ብዙሃነታችን በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ሙከራን በመከላከል ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ የተሳተፉ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት መልካም እሴቶቻችንና አብሮነታችን የኢትዮጵያ መገለጫ በመሆኑ ይህን እሴት ለማስቀጠል የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

በትዕግስት ቶሎሣ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here