የግንቦት 20 28ኛ አመት በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር የችግኝ ተከላ ተካሄደ

0
617

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንደ ሀገር በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መሠረት እንደ ድሬዳዋ አስተዳደርም ከከፍተኛ አመራር እስከ መካከለኛ አመራር እንዲሁም ማህበረሰቡ በችግኝ ተከላው ተካፍለዋል፡፡

የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ መሀዲ ጊሪ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ከተማችንን ውብና ፅዱ በማድረግ አረንጓዴ ልማትን ለማስቀጠል ሁሉም የማህረሰብ አካላት የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

የድሬዳዋ የኢህኤግ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ግዛው ባስተላለፉት መልዕክት ከተማችን ብሩህ ተስፋ ያላት ከተማ በመሆኗ የሰላም፣ የመቻቻል የፍቅር እሴታችን በማጎልበት አስተሳሰባችን እንደተከልነው ችግኝ ለምልሞ ከብሔር፣ ከዘር ተላቀን መጥፎ አስተሳሰብን በማስወገድ ከተማችንን እናልማ ብለዋል፡፡

የኢህኤግ ፅ/ቤት ሀላፊ አክለውም በድሬደዋ የባቡር ፣የኢንተርናሽናል አየር መንገድና ወደብ እንዲሁም የክፍያ መንግዶች በመኖራቸው ለወጣቱ የስራ እድል መፍጠር ያስችለናል ብለዋል ፡፡

 በችግኝ ተከላው የተሳተፉ የማህበረሰቡ ክፍልም በሰጡት አስተያየት ከጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ የተላለፈውን መልእክት በመቀበል እኛም ከተማችንን በማስዋብ የድርሻችንን መወጣት አለብን ብለዋል ፡፡

በችግኝ ተከላው መረሀ ግብር ከዛሬ ጀምሮ  ክረምቱን በሙሉ ሁሉም የአስተዳደሩ ማህበረሰብ እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here