የሀገር አቀፍ እና አስተዳደራዊ ፈተናዎች ማስፈፀሚያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

0
496

     በንቅናቄ መድረኩ የትምህርቱ ዘርፍ ባለድርሻ አካላትና የተማሪ ወላጆች እንዲሁም የፀጥታ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። በ2011ዓ. ም የትምህርት ዘመን ከሰኔ 3-5 የ10 ክፍል ተፈታኞች 4795 ከሰኔ 6-11 የ12ክፍል ተፈታኞች 1560 ከሰኔ 12-14 የ8 ክፍል ተፈታኞች 7070 በአስተዳደሩ በአጠቃላይ 13 ,425 ተፈታኞች እንደሚፈተኑ ተገልፃል።

    ፈተናው የተሳካ እንዲሆን በአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ የሚመራ ኮማንድ ፖስት ተዋቅሮ ስራ መጀመሩንም ከመድረክ የተገለፀ ሲሆን 1500 የሚሆን የሰው ሃይልም ፈተናውን ለማስፈፀም ዝግጁ መደረጉን የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ  ሙሉካ መሀመድ አሳውቀዋል፡፡

 

    የፈተና ጉዳዮች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ካሳሁን ማሞ ፈተናውን በሰላማዊ ሁኔታ ማካሄድ እንዲቻል ከባለ ድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል በሚል እንዲሁም  ለርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እንደ መመሪያ የሚያገለግል ሰነድ ለውይይት አቅርበዋል፡፡

   በውይይቱም ተሳታፊ የነበሩት ርዕሰ መምህራን፣ የተማሪ ወላጆች፣ ከየቀበሌው የመጡ የትምህርት ማስተባበሪያ ኃላፊዎች፣ ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም የመሰረታዊ መምህራን ማህበር አባላት በሰነዱ ላይ ያላቸውን ሃሳብና አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡

   በመጨረሻም ለተነሱት ሃሳብና አስተያየቶች ወ/ሮ ሙሉካ ምላሽ ሰጥተው፤ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካል የወሰደውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ትእዛዝ በመስጠት መድረኩ ተጠናቅቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here