የአስተዳደሩ አስፈፃሚ አካላት የመንግስት ንብረት አያያዝና አጠቃቀም ላይ ይበልጥ መሻሻል እንዳለበት ተገለፀ።

0
466

በድሬዳዋ አስተዳደር የተቋማት ንብረት አያያዝ ዙሪያ የመስክ ጉብኝት ያካሄደው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግከሎት ጽ/ቤት በቢሮ ኃላፊ በተመራ ልዑካን ቡድን የድሬደዋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ምልከታውን ባካሄደበት ወቅት አገልግሎት የማይሰጡና ለአስተዳደሩ ገቢ ማስገንኘት ያለባቸው ንብረቶች ቀላልና ከባድ ክብደት ያላቸው የብረታ ብረት ቁሳቁሶች፣ ለኮሌጁ ቅጥር ጊቢ ንጣፍ ቀርበው የተከማቹ የንጣፍ ሸክላዎች እና በአያያዝ ክፍተት ለአደጋ የተጋለጡ ንብረት ክፍል የሚገኙ የመገልገያ እቃዎችን የተመለከተ ሲሆን በበጀት አመቱ ቀሪ ሁለት ወራት ኮሌጁ የማያገለግሉትን እንዲያስወግድና የተከማቸው የሸክላ ንጣፍ እንዲነጠፉ እንዲሁም በንብረት ክፍል ያሉ ንብረቶች በአግባቡ እንዲያዙ የአሰራር ሂደቱን በመከተል ሊሰሩ እንደሚገባ ሉኡካን ቡዱኑ ገልፀዋል፡፡

 

 ሉኡካን ቡድኑ በማስከተልም የግብርና ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የንብረት አያያዝ በጎበኙበት ወቅት ካለአገልግሎት የቆሙ አሮጌ የውሃ መሳቢ ጄኔሬተሮች 2 ሞትር ሳይክሎች፣ 1 ተሽከርካሪ እና ብረታ ብረቶች ያለአገልግሎት በመቀመጥ መባከናቸውን ተመልክቷል ። የንብረት ክፍል አያያዙ የተሻለና በጥሩ ሁኔታ ላይ ቢሆንም ቡድኑ በንብረት አያያዝ ላይ የሰጣቸውን ግብረ መልስ በመቀበል የመጠቀሚያ ጊዜያቸው እያለፈ የሚገኙ ግብዓቶች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው በበጀት አመቱ ቀሪ ሁለት ወራት የማያገለግሉ ንብረቶች የማስወገድ ስራ በትኩረት እንደሚሰሩ ከጉብኝቱ በኋላ ባካሄዱት ውይይት የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here