በቀበሌ 02 አስተዳደር መስቀለኛና ገንደተስፋ የነበረው ግጭት የእርቅ ስነ-ስርአት ተካሄደ፡፡

0
443

በድሬዳዋ አስተዳደር በቀበሌ 02 አስተዳደር ግንቦት 07/2011 ዓ.ም በመንደር የተነሳው ግጭት የእርቅና የሰላም ኮንፍረንስ ተካሄደ፡፡

በቀበሌ 02 አስተዳደር  ከፅዳት ዘመቻው ጎን ለጎን በዘላቂነት የክፋትን ሴራ ለማፅዳት በመስቀለኛና በገንደተስፋ መንደር የነበረን የእርስ በእርስ ግጭት የአካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች በተገኙበት የእርቅና የሰላም ኮነፍረንስ ተካሄዷል፡፡

 

በኮንፈረንሱ የተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በአካባባያቸው ሰላም እንዲሰፍን ላደረጉላቸው የፀጥታ ሃይሎች ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ እንደዚህ አይነት ግጭቶች እንዳይከሰቱ የህግ የበላይነት ሊረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

በነበረው ግጭት የውደሙ ንብረቶችና የደረሱ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳቶችን ጊዜያዊ በተዋቀረ ኮሚቴ  ተፈትሸው ለተሳታፊዎች በሪፖርት ቀርቧል፡፡

በኮንፍረንሱ የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች በመገኘት በሁለቱ መንደር የሚኖሩትን ማህበረሰቦች ሀይማኖታዊ ትምህርት በመስጠት የእርቅ ስነ ስርአቱን አካሂደዋል፡፡

በመጨረሻም የሁለቱ መንደር ወጣቶችና ማህበረሰቡ አንገት ላንገት በመተቃቀፍ የኢትዮጵያ እሴት የሆነውን አብሮነትና አንድነት  አንፀባርቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here