ሁለተኛ ሀገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ በድሬደዋ ከተማ ተካሄደ

0
489

በድሬደዋ ከተማ በጠቅላይ ሚኒሰተር ዶ/ር አብይ አህመድ በተላለፈው መልእክት መሰረት የተለያዩ አመራሮች፣ ነዋሪ ህብረተሰብ እና የሰራዊት አባላት እንዲሁም የቆሻሻ አስወጋጅ ማህበራት ተሳትፈዋል፡፡

 

በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ዘረኝነትን እንፀየፋለን አብሮነትን እናከብራለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል፡፡

የድሬደዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ በጽዳት ዘመቻው ላይ እንደተናገሩት ቁሻሻን ከቤታችን እንደምናስወግደደው ሁሉ በውስጣችን ያለውን ክፉ አስተሳሰብ ከልባችን አውጥተን ውስጣችንንም ልናጸዳው ይገባል ብለዋል፡፡

በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ የሰራዊት አካላት በሰጡት አስተያየት ከጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላለፈውን መልዕክት በመከተል የድሬደዋን ቁሻሻ ብቻ ማጽዳት ብቻ ሳይሆን በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የብሄር ፣ የዘረኝነት የክፋት አስተሳሰብን ልክ እንደ ቁሻሻው ተጠርጎ እንዲወጣ ከህብረተሰቡ ጎን በመሆን አጋርነታችንን ማሳያ ነው በማለት የሀገርና የአካባቢዋን ሰላም ለማስጠበቅ በምናደርገው ጥረትም ህብረተሰቡ ከጎናቸው እንዲሆን  ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here