29 ኛው አመት የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የምስረታ በአል በድሬዳዋ አስተዳደር እስታዲም በድጋፍ ሰልፍ ተከበረ፡፡

0
727

 የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦ.ዴ.ፓ) በኦሮሚያ ክልል ዲሞክራሲና ልማት እንዲረጋገጥ ከማድረጉም  ባለፈ በድሬደዋ አስተዳደርም ከእህትና አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በርካታ ስራዎች መስራታቸው ተገለፀ፡፡

“አንድነትና መደማመጥ ለተሻለ ድል” በሚል መሪ ቃል 29 ኛ አመት የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የምስረታ በአል በድሬዳዋ አስተዳደር ስታዲየም በድገፍ ሰልፍ ተከብሯል፡፡ በስነስርዐቱ ላይ ተገኝተው  ንግግር ያደረጉት በድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ መሀዲ ጊሬ እንዳሉት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦ.ዴ.ፓ) ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ሠላም፣ ዲሞክራሲና ልማት እንዲረጋገጥ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ በርካታ ድሎችን ከማስመዝገቡም ባለፈ በድሬደዋ አስተዳደርም ከእህትና አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በርካታ ስራዎች መስራታቸውን አቶ መሀዲ ጊሬ ተናግረዋል፡፡

ኦ.ዴ.ፓ  የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎትና ጥቅም ለማስጠበቅ መራር ትግል ሲያደርግ የቆየና በርካታ ፈተናዎችን ያለፈ ፓርቲ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀር ገልፀው ኦ.ዴ.ፓ ባደረገው ትግልም የኦሮሞ ህዝብ የሚገባውን እንዲያገኝ ለማድረግ በከፈለው መስዋት የዛሬውን ድል ማስመዝገቡን አቶ ከድር  ተናግረዋል፡፡

 

አሁን የተገኘውን ለውጥ ብሎም በፖለቲካውም ዘርፍ የተመዘገበውን ድል በኢኮኖሚውም መስክ ለመድገም  ከየትኛውም ጊዜ በላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን ቃል በምንገባበት ወቅት በአሉ መከበሩ ለየት እንደሚያደርገው በድሬዳዋ የኦ.ዴ.ፓ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልጁዋድ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

የኦ.ዴ.ፓ የምስረታ ክብረ በአል ላይ የተገኙት የድርጅቱ ደጋፊዎችና አባላት በበኩላቸው ኦ.ዴ.ፓ ባለፉት አመታት በሰራቸው በርካታ የልማት ስራዎች ውጤት መመዝገብ መቻሉን ተናግረው አሁን ላይ የተገኙትንም ውጤቶች በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር በተከበረው 29 ኛ አመት የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የምስረታ በአል ላይ እህት ድርጅቶች የእንኳን አደረሳቹ መልእክት አሰተላልፈዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here