የኦሮሞ የቋንቋና ባህል ማበልፀጊያ ክበብ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተቋቋመ

0
920

ቋንቋዎችን፣ባህላችን እሴቶቻችንና ታሪካችንን ጠብቀን ለመጪው ትውልድ ማስረከብ የአሁኑ ትውልድ ግዴታ ነው፡፡ በሚል መሪ ቃል የኦሮሞ ቋንቋና ባህል ባበልፀጊያ ክበብ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተቋቋመ፡፡

ክበቡ የኦሮሞ የቋንቋና ባህል በማስተዋወቅ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበረውን ፍቅርና ሰላም እንዲሁም አብሮ የመኖር እሴትን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ ክበቡ ጠንክሮ እንደሚሰራም እምነታቸው እንደሆነ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ተናግረዋል

ክበቡ  በዩኒቨርሲቲው በተቋቋመበት እለትም ታዋቂ የአፍረን ቀሎ አርቲስቶች ፣ አባገዳዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተሳተፉ ሲሆን የኦሮሞ ባህልን ከማስተዋወቅ አንጻርም የባህል ምግቦች የተለያዩ ብሄሮች ብሔረሰቦች አለባበስ ትዕይንት ተካሂደዋል፡፡

 

እንዲሁም የኦሮሞ ቋንቋ ባህልና ታሪክ ላይ የተመሰረተ ጥናታዊ ፅሁፍ በዶ/ር ተሾመ ኤገሬ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የኦሮምኛ ቋንቋ ዲፓርትመንት ኃላፊ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ተማሪ እና የክበቡ መስራች ተማሪ ቢቂላ ገሮምሳ በበኩሉ እንደተናገረው በክበቡ ሀይማኖት ተኮር ነገሮችን ማንፀባረቅና ከማንኛውንም ፖለቲካ አመላካከት የጸዳ መሆኑን በመግለጹ የኦሮሞ ባህልን ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በማዋሀድ ልምድ ልውውጥ በማድረግ በልዩነታችን ውበት አንድነታችን የሚካሄድበት ክበብ ነው ብሏል፡፡

በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ህብረት ስር ክበቦች ለማደራጀት በሚቻለው መሰረት የኦሮምኛ ቋንቋና ባህልን ለማበልጸግ እንደ አንድ ክበብ ሆኖ የኦሮምኛ ቋንቋና ባህል ክበብ ሚያዝያ 5/2011 ቅዳሜ ተመስርቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ከተለያዩ ብሄር በሄረሰብ በመምጣታቸው የራሳቸውን ቋንቋና ባህል ለማስተዋወቅ ክበብ ለመመስረት ቢነሱ ዩኒቨርሲቲው እኩል ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here