በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 5ተኛ አገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡

0
734

በአገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ “የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ሁሉን አቀፍ ለሆነ እድገት፡፡” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄዷል፡፡

 

በኮንፈረንሱ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ መካሄድ ልምድ ለመለዋወጥ ዋና ድልድይ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ያሬድ ማሞ ገለፃ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማርና የምርምር ስራዎችን እንዲሁም የማህበረሰቡ አገልግሎት ሰጪዎች በመሆናቸው የምርምር ስራዎችን በተለያዩ ዘርፎች ላይ በማድረግ ለማህበረሰቡ አገልግሎት መፍሄ ያመላክታል እንዲሁም ለፖሊሲ ቀረፃም ትልቅ ግብዓት ነው ብለዋል፡፡

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ሊበን 5ተኛ ሀገር አቀፍ የምርምር ስራዎች በተለያዩ ዘርፎች ላይ ምርምር መደረጉን ገልፀው የምርምር ስራዎቹ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እነዲሰጡ በመፅሐፍትነት በአዲስ ታትመው ይሰራጫሉ ብለዋል፡፡

የምርምር ስራዎች እውቀት መጨመርና ምርታማነትን በመጨመር ቀልጣፋ የሆነ አሠራር ማምጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል ዶ/ር ጌታቸው  ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here