በድሬዳዋ ከተማ የፅዳተው ዘመቻ ተካሄደ

0
853

ከማለዳው ጀምሮ ሀገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻና የ5 ኪ.ሜ የእግር ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው የፅዳት መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ መሐዲ ጊሬ እና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራርና አባላቶች፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የታዳጊ ፕሮጀክት ሰልጣኞች ሌሎች የማህበረሰብ ክፍል ተሳትፈዋል፡፡

የጠ/ሚ/ር  ዶ/ር አብይ አህመድ መልእክት በመቀበል በድሬዳዋ አስተዳደር መነሻውና መድረሻውን ምድር ባቡር አደባባይ በማድረግ የፅዳትና የ5 ኪ.ሜ የእግር ጉዞ የተሳተፉት የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ መሀዲ ጊሬ ባስተላለፉት መልዕክት አካባቢያችንን ስናፀዳ በእዕምሮአችን ውስጥ ያለውን የብሄርተኝነትና ክፉ አስተሳሰብ አብረን ማፅዳት አለብን ብለዋል፡፡

ም/ከንቲባ አቶ መሐዲ ጊሬ ከዚህም ጋር አያይዘው በየወሩ ይህንኑ ተግባር በማከናወን የሀገራችን ሰላም ለማስከበር ከፀጥታ አካላት ጋር ህብረተሰቡ በጋራ በመሆን የሀገራችን ሰላም መጠበቅ ይኖርብናል ብለዋል፡፡

 

የድሬዳዋ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ዑመር በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ቆሻሸን ጠርገን እንዳፀዳን ሁሉ ጎጠኝነትን፣ ጎሰኝነትን፣ ብሔርተኝነትን አስተሳሰብ ከውስጣችን በማውጣት እንደ ቆሻሻው በመጣል ድሬዳዋ ቀደም የምትታወቅበትን ፍቅሯን ለመመለስ በውይይት በመግግባባት አንድነታችንና አብሮ የመኖር እሴቶችን የመመለስ ኃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡

የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ወ/ሮ ስንታየሁ ደባሳ በበኩላቸው እንደ ሀገር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን እየተበራከቱ በመምጣታቸው ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅሰድቃሴ ልምድ እንዲያዳብር በሚል መሪ ቃል በወር 1 ቀን ከትራፊክ ነፃ መንገድ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የአስተዳደሩም ጤና ቢሮ ከዚህ ጋር በማያያዝ በሚል ዶ/ር አብይ አህመድ ባስተላለፉት መልእክት የጤና ተቋማት ንፁህና ማራኪ እንዲሆኑ የፅዳት ዘመቻው በጤና ተቋማት እና ከተማዋን በማፅዳት ማክበራቸውን ገልፀዋል፡፡

በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉት ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት አካባቢያቸውን በማፅዳት ሀገራችንን ሰላሟን የነሳትን ብሄርተኝነት እና ክፉ አስሳሰብን አብረን ከልባችን በማውጣት ሰላማችን አስጠብቀን መኖር ይገባናል ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here