የህዳሴ ግድብ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚያደርጉትን አስተዋጽዎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች ገለጹ

0
788
  • የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 8ተኛ አመት በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በአገራችን እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ሲሆን ይህም ፕሮጀክት በመንግስትና በመላው የሀገራችን ህዝቦች በጋራ እየተገነባ ይገኛል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 8ተኛ አመት በዓል አከባበር “ታላቁ ህዳሴ ግድባችን የአንድነታችን ህብረ-ዜማ የለውጣችን የድል አርማ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ስነ-ስርዓቶችና በአስተዳደራችን ደግሞ በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀር ከተማ አስተዳደሩና መላው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ባለፉት ሰባት አመታት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በቦንድ፣ በስጦታና በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያዎች ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን ሲያበረክቱ መቆየታቸውንና በዚህም ከ81 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማድረግ መቻሉንም አቶ ከድር ገልፀዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የሚኖሩ ነዋሪዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ችግሮች እንኳን ቢያጋጥሙ ለችግሮቹ መፍትሄ በማስቀመጥ ፕሮጀክቱን እስከ ፍፃሜው ለማድረስ በጋራ እንደሚሰሩ የድሬዳዋ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የህዝብ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ከፈለኝ አበራ አብራርተዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠበት እለት አንስቶ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረው ፕሮጀክቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስም የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚያበረክቱም አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱ ላይም ባለፉት ሰባት አመታት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የህዝቡ ተሳትፎ ብሎም በሜጋ ፕሮጀክቱ ላይ አጋጥመው የነበሩ ችግሮችና በቀጣይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ዳግም እንዳይከሰቱ የተቀመጡ መፍትሄዎች ላይ የሚዳስሱ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here