የሴቶች ቀን በአስተዳደሩ በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡

0
719

በድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግና አመራር ሰጪነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰራ የአስተዳደሩ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ገለፀ

በአለም አቀፍ ደረጃ 108 ጊዜ በሀገራችን ለ43 የሴቶች ቀን ተከብሯል “የላቀ  ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በሚል” መሪ ቃል ሴቶች ቀን በአስተዳደሩ ሲከበር የድሬዳዋ አስዳደር የሴቶች ህፃናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንዳሉት በድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶችን አመራር ሰጪነት ለማሳደግና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት እንሰራለን ብለዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም ሴቶች በአንድነትን ተባብረን ሰላምን ለመስበክ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ጠቅሰው እናቶች ልጆቻቸውን በመምከርና ማህበራዊ ግንኙነትን በማሳደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉ ሴቶች እንዳሉትም ሴቶችን ለማብቃት እራሳቸውን ያጠናከሩ ሴቶች ሌሎችን መርዳት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ሰላምና አንድነትም በተመለከተም ብዙ ይጠበቅብናል ያሉት አስተያየት ሰጪዎች እነሱም የድርሻቸውን አንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here