“ጉዞ ሉሲ ለሠላምና ለፍቅር” በድሬዳዋ የነበራት ቆይታ አጠናቃለች፡፡

0
926

ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ፌስቲባል በድሬዳዋ ከተማ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ለተማሪዎች አነቃቂ ንግግር የቀረበ ሲሆን ንግግሩን ያደረጉት ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ ሰዎች የሀሳባቸው ነፀብራቅ ናቸው፡፡ በመሆኑም ወጣቱ ትውልድ ለሀገሩና ለራሱ በሚጠቅም ሀሳብ ሊጠመድ ይገባል ብለዋል፡፡

ረዳት ፕሮፌሰሩ ወጣቱ ትውልድ በሕይወቱ ምንም አይነት ውጣ ውረድ ቢገጥመውም ውጣ ውረዱን ተቋቁሞ ለአላማ መኖር ይገባዋልም ብለዋል፡፡

በመድረኩ የአለም ታላላቅ ሰዎች የሕይወት ተሞክሮ ለወጣቱ ለማስተማሪያነት ተነስቷል፡፡ በየትኛውም ሀገር የወደፊት እጣ ፈንታ ወሳኝ ወጣቶች በመሆናቸው የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ሕይወት ለመለወጥ ከሚያደርጉት ጥረት በዘለለ ለሀገር የሚጠቅሙ በመሆናቸው በርትተው መማር እንዳለባቸው ተገልፃል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የወደፊት ህልማችሁን እውን የምታደርጉበት ቦታ በመሆኑ የምታነሱት ሀሳቦች ለዩቨርሲቲው ማህበረሰብ የሚጠቅም መሆን አለበት እንዲሁም የኔ የሚለውን ትተን የኛ የሚለውን ሀሳብ ማራመድ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

ክልላዊት የአስተዳደር ወሰን፣ የብሄር ጉዳይና የማንነት መግለጫ እንጂ የአብሮነታችን ገደቦች አይደሉም፡፡ በሚል መርህ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ወደ አዋሳ አቅንታለች፡፡

በትዕግስት ቶሎሣ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here