‹‹ደንበኞቻችን ቅሬታ ይዘው የሚመጡ መሆናቸው ስራችንን ከባድ ያደርገዋል፡፡›› ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የህዝብ የቅሬታና አቤቱታ ሰሚ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የመልካም አስተዳደር እጦት ነዋሪውን ለቁጣ አነሣሥቶታል የአስተዳደሩ ነዋሪዎች

0
973

ላይ ከፍተኛ የሆነ መንጓተት አለበት፡፡ ይሄም ነዋሪውን አስቆጥቷል ይላሉ፡፡

     የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰጡት ግልጋሎት ተደራሽና ለህዝብ አጥጋቢ እንዲሆን የማድረግ ስራዎችን ማሣለጥ፣ ህዝብ የተሰማውን ስሜት በግልፅ የሚናገርበትና ቅሬታውን የሚያሰማበት ሁኔታን ማመቻቸት፣ ከቅሬታ አቅራቢው ቅሬታውን ሰምቶ ቅሬታ ከቀረበበት ጋር በመገናኘት ለጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥ ማስቻል የድሬዳዋ አስተዳደር የህዝብ የቅሬታና አቤቱታ ሰሚ ዳይሬክቶሬት ከሚሰራቸው ስራዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

     እኛም በዚህ ቢሮ ላይ ከሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ያልናቸው የባለሞያዎች በስራ ሰዓት በቢሮ አለመገኘት፣ የአቅም ክፍተት መኖርና ችግሮችን ሰምቶ በፍጥነት ምላሽ ያለመስጠት እንዲሁም የተለያዩ በህዝብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ይዘን የዳይሬክቶሬቱን ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ምላሽ እንዲሰጡን ጠይቀናል፡፡

     ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ከህዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ያን ያህል የጎላ የአቅም ማነስ ክፍተት ባይኖርም በየጊዜው ባለሞያዎችን በተለያዩ ስልጠናዎች በመደገፍ ብቁ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው፤ በተለይም ባለሞያዎች በስራ ገበታቸው አይኖሩም የተባለበት አግባብ ግን ትክክል እንዳልሆነና በባለጉዳይ ቀናት ብቻ ቅሬታ የሚቀበሉ መሆናቸውን በመጠቆም በነዚህ ቀናት ቅሬታን ማቅረብ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ በመረጃ የቀረቡትን ጥያቄዎች በአካል ተገኝተው ማየት ስለሚኖርባቸው የስራው ባህሪ ቢሮ ውስጥ የማያስቀምጥ መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲረዳም ጠይቀዋል፡፡

     በአንዳንድ ተቋማት የዳይሬክቶሬቱን ኃላፊነት ዝቅ አድርጎ የማየት ችግር ስራቸው ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ ይህንንም ችግር በአሰራርና በአደረጃጀት እንዲሁም በውይይት በቅርብ ጊዜ እንደሚስተካከል ሙሉ እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

     ህዝብ የሚያነሳቸው ችግሮች እውነት መሆናቸውን ያመኑት ኃላፊዋ አመራሩ በሙሉ አቅሙ እንደ መሪ በትክክል ከመራ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንደሚቻል ነው ኃላፊዋ  የተናገሩት፡፡

     ከተለያዩ ተቋማት በደል ደርሶባቸው የሚመጡ ደንበኞችን ስለሆነ የምናስተናግደው እኛ ጋር እርካታን ካላገኙ ነገሮች ስለሚባባሱ ስራችንን ከባድ ያደርገዋል ያሉት ወ/ሮ ፈጡም የመንግስት የአሰራር ክፍተቶች፣ የአመራሮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አለመወጣት፣ ከቅጥር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮች፣ የመሬት ልማት በይዞታ ማረጋገጫና ድንበር አከላለል ላይ የሚነሱ ሮሮዎች ጊዜ የሚፈጁ እንዲሁም መረጃና ማስረጃን መያዝና ወርዶ ማየት የሚፈልጉ በመሆናቸው ጊዜ ወስደን በጥንቃቄ ለመስራት የሚፈጀው ጊዜ ታውቆ ህብረተሰቡ ለዚህም ትእግስት እንዲኖረው ጠይቀዋል፡፡

     ሌላው በፍርድ ቤት የተያዙና ልናያቸው የማንችላቸውን ጉዳዮች በማምጣት ችግሬ አልተፈታም ብሎ ቅሬታ የማሰማት አዝማሚያዎች እንዳሉም ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በቀበሌ ደረጃ የሚፈቱ ችግሮችን ማእከል ድረስ ይዞ መምጣትም ሌላው ጊዜን ከሚፈጁ አቤቱታዎች መካከል በመሆናቸው ማህበራዊ ኑሮ ላይም ቀውስ ስለሚፈጥር ህብረተሰቡም ሆነ በየደረጃው ያለው አመራር በቅንጅት ስራዎችን ለመስራት ፍቃደኛ ቢሆን ችግሮች ተባብሰው ጠብና አምባጓሮ መፍጠር ደረጃ እንደማይደርሱ ወ/ሮ ፈጡም በምላሻቸው አንስተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here