ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በጀግጀጋ ከተማ የከተሞች ፎረም ኤግዝብሽን ጎብኝተዋል፡፡

0
1193

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለሚገነባው (የአመንጄ የጎል)የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል ፡፡

 ቀዳማዊት እመቤቷ በጽህፈት ቤታቸው በኩል ከሚሰሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ከረጂ ድርጅች በሚያገኙት ገንዘብ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን መገንባት ነው፡፡

 በ20 ሚሊዮን ብር የሚገነባው የ2 ደረጃ ትምህርት ቤቱ የግንባታው ወጪ በኤ.ፌ.ድሪ ቀዳማዊት ጽህፈት ቤት እንደሚሸፈን ተናግረዋል ፡፡

 ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ -ስርዕት ላይ እንደገለፁት ትምህርት ቤቱ በአንድ አመት ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ብለዋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤቷ ቀደም ሲልም በአማራ፣ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች በተመሳሳይ መልኩ የትምህርት ቤቶች ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸው የሚታወስ ነው ፡፡

በጅግጅጋ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የከተሞች ፎረም ኤግዝቢሽን ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ጎብኝተዋል ፡፡

በሱማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ በበኩላቸው ቀዳማዊት እመቤት በሀገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎ የትምህርት ቤት ግንባታዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ጋር አያይዘው ርዕስ መስተዳድሩ በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ የመሰረት ድንጋይ በቀዳማዊት እመቤቷ የተቀመጠው ትምህርት ቤቱ መገንባቱ ለአካባቢው የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነት ጠቀሚታው የጎላ መሆኑም ነው የገለፁት፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here