በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ማህበረሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡

0
795

የኢትዮጵያ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ ባለድርሻ እና አጋር አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰቷል፡፡

ለተከታታይ 5 ቀናት ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል በወጣው አዋጅ ቁጥር 909/2007 እና በአዲሱ የውጭ አገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቶ አወያይቷል፡፡

በፌደራል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ህገወጥ የሠራተኛ ምልመላ መከላከያ ቡድን መሪ አቶ ዘሪሁን የሺጥላ በውይይት መድረኩ እንደተናገሩት ሰዎች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ህገመንግስታዊ መብታቸው ስለሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ህግና ስርዓትን መሠረት ባደረገ አግባብ መንቀሳቀስ የሚያኖርበትን ሁኔታ በህግ በተደገፉ አግባብ   አዋጅ ቁጥር 923/2008 የኢትዮጵያ የውጭ አገር የስራ ስምሪት የወጣ በመሆኑ በዚያ ተጠቅመው ምን አይነት መስፈርት እንደሚያስፈልጋቸው ከየት ተነስተው ምን አምልተው መሄድ ይኖርባቸዋል የሚለውን ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል ፡፡

የቡድን መሪው አያይዘውም በውጭ አገር የስራ ስምሪት አዋጅ ውስጥ የ8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች አጠቃቀም ስልጠና ማግኘት፣ የብቃት ምዘና ማረጋገጥ ፈተና፣ በቋንቋቸው ትምህርት እንዲያገኙ እና ከመሄዳቸው በፊት የቅድመ መንገድ ገለፃ ያካተተ ሲሆን በአዲስ አበባ ብቻ ሲካሄድ የነበረውን ወደታች በማውረድ በክልሎች እና በድሬዳዋ ለማስተግበር ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉ ተሳታፊዎችም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በተሻሻለው አዋጅ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡ ከተነሱት ሀሳቦችም ዜጎችን ከገጠር መልምሎ የሚያመጡ ደላሎች ላይ ጥቆማ አለማድረግ፣ ይዘው ለመሰደድ ያሰቡትን ገንዘብ በሀገራቸው ሰርተው እንዲለወጡበት ትምህርት አለመስጠት ክፍተቶች እንዳሉ ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡

ለተጠየቁ ጥያቄዎች ከመድረኩ በተሠጡ ምላሾችም ማህበረሰቡ ይህንን እንደባለቤትነት ባለማየቱ እና የመንግስት ስራ ብቻ አድርጎ በማሰቡ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እየተባባሰ መቷል፡፡ ለዚህም ማህበረሰቡ የድርሻውን በመወጣት ከመንግስት ጎን በመሆን ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here