የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት 2007 ዓ/ም የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት

0
1021

የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም በተመለከተ 
ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ረገድ በአስተዳደራችን የተነደፈውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት በማድረግ ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ከማስመዝገብ አንጻር በተደረገው ፈረጀ ብዙ የልማት እንቅስቃሴ ባለፉት አራት ተከታታይ አመታት በአጠቃላይ ኢኮኖሚው የ11.8 በመቶ አማካይ አመታዊ እድገት ተመዝግቧል፡፡ በ 2005 ዓም የተመዘገበው እድገት ለብቻው ሲታይ የ 11.9 በመቶ ሲሆን የየዘርፉ አስተዋጽኦ ሲታይ ግብርና በ13 ፣ኢንዱስትሪ በ 13 እንዲሁም አገልግሎት በ 10 በመቶ እድገት ተመዝግቦዋል፡፡ የኢኮኖሚ መዋቅሩም ሲታይ ግብርና 10 ፐርሰንት፣ኢንዱስትሪ 33፣እና አገልግሎት 57 ፐርሰንት ላይ እንዲገኝ አድርጎታል፡፡ በያዝነውም የበጀት ዓመት ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው በ11.5 በመቶ ያደጋል ተብሎ የሚጠበቅ ከመሆኑም ባሻገር ከኢኮኖሚ መዋቅር አንጻርም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ በተቀመጠው መሰረት ግብርና ወደ 12 ፐርሰንት፣ኢንዱስትሪው ወደ 40 ፐርሰንት እና አገልግሎት ወደ 48 ፐርሰንት እንዲደርስ በመተግበር ላይ ሲሆን በተለይ በኢንዱስትሪው ዘርፍ በፌደራል መንግስት የተለየ ኢንዱስትሪ ዞን ጥናት የተጠናቀቀ ከመሆኑም ባሻገር ፣ የደረቅ ወደብ ግንባታ ፣የአይሻ ደወሌ የአስፋልት መንገድ ግንባታ መጀመር እና ድሬዳዋ የምስራቅ ኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ማእከል እንድትሆን ተልዕኮ የተሰጣት በመሆኑ በቀጣይ በኢንደስትሪ ረገድ ለታቀደው እቅድ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡

በመሆኑም በአጠቃላይ ይህ የተመዘገበው እድገት እንደሚያሳየው ለአራት ተከታታይ አመት ባለ ሁለት አሀዝ እና ከተቀመጠው አነስተኛ የእድገት አማራጭ ከፍ ያለ እድገት እየተመዘገበ እና የሚመዘገብ መሆኑ ካለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት እና የተያዘው ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸምን በማየት ማሳካት እንደተቻለ እና እንደሚቻል ከወዲሁ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ 
የነብስ ወከፍ ገቢን በተመለከተ፤ በመንግስትና በግል ባለሀብቱ እየተደረጉ ባሉ ስራዎች የአስተዳደሩ አጠቃላይ ኢኮኖሚበ2002 ዓም ከነበረበት 3.0 ቢሊየን ብር በ2006 ዓም ወደ 6.3 ቢሊየን ብር እንደደረሰ የሚገመት ሲሆን ይህም የነብስ ወከፍ ገቢው በ2002 ዓም ከነበረበት 628 የአሜሪካን ዶላር በ2006 ዓም ወደ 806 ዶላር ደርሶዋል ፡፡ 
የስራ አጥነት በተመለከተ፤ የስራ አጥነት ምጣኔ በአስተዳደር ደረጃ ገጠርና ከተማን ጨምሮ በ2002 ዓም ከነበረበት የ28 ፐርሰንት በ2006 በጀት ዓመት በመንግሰት እና በግል ባለሀብቱ እንቅስቃሴ ወደ 14.9 በመቶ ዝቅ እንዲል ሆኖዋል፡፡ በተያዘው የበጀት ዓመትም ወደ 12 ዝቅ ለማድረግ በርካታ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡የስራ አጥነት ምጣኔው በገጠር እና በከተማ ተለይቶ ሲታይ በገጠር ከ12 ወደ 2.5 በመቶ የወረደ  ሲሆን በከተማ ከ28 ወደ 22.3 በመቶ ዝቅ ያለ ሲሆን ይህንንም በተያዘወው በጀት ዓመት ወደ 20 ፐርሰንት እንዲወርድ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ረገድ በ2007 በጀት አመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት በአጠቃላይ ለ7470 ቋሚእና ለ9029 ጊዜያዊ በአጠቃላይ ለ16499 የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ ይህ አፈፃጸም በስድስት ወር ውስጥ ሊሰራ ከተቀደው አንጻር 96 እና 174 ፐርሰንት የሚያመለክት እጅግ አበረታች አፈጻጸም ሆኗል፡
የአስተዳደሩ ገቢ አሰባሰብን በተመለከተ፤የአስተዳደሩን የልማት ዕቅድ በማቀናጀት፣ ዘመናዊ የፋይናንስ አስተዳደር በማስፈን፣ የግብር ከፋዩን ህብረተሰብ የልማቱ አጋዥ ኃይል በማድረግ፣ የገቢ አቅማችንን በማሳደግ፣ ያለውን ውሱን ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል፣ የፈጣንና ዘላቂ ልማት ባለቤት የመሆን ውጤትን ደረጃ በደረጃ ለማሳካት በርካታ ተግባራት ተከናውነው ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ 
የአስተዳደራችንን ገቢ የመሰሰብሰብ አቅም በአምስቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት በ2002 ከነበረበት 135 ሚሊዬን ብር ወደ479 ሚሊዮን ብር ታቅዶ በተያዘው 2007 የበጀት አመት ስድስት መቶ ሀምሳ ሚሊዬን ብር ለመሰብሰብ የሚያስችል አቅም ላይ ደርሷል፡፡ በዚህ የመሰብሰብ አቅም ላይ በመመስረት ባለፉት የ2007 ዓም ስድስት ወራት በአጠቃላይ ገቢ ብር324.3 ሚሊዮን ለመሰብሰብ ታቅዶ፤ የ6 ወራት አፈፃፀም335.7 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም ከዕቅዱ አንፃር 103.52 ፐርሰንት አፈጻጸም ያመለክታል፡፡ ይህ ውጤት ከ2006 ዓ.ም ተመሳሳይ የ6 ወራት ገቢ ጋር ሲነፃፀር በ 65.53 % የገቢ ብልጫ የተመዘገበበት ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል የአስተዳደሩ ገቢ በየአመቱ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም ኢኮኖሚው ሊያመነጭ የሚችለውን ያህል ገቢ ማሰባሰብ እና እያደገ የመጣውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የመቻል ጉዳይ በቀጣይ በትኩረት ተጠናክሮ የሚሰራባቸው ይሆናል፡፡
የአስተዳደሩ ጠቅላላ ወጪ አፈጻጸም በተመለከተ፤ የአስተዳደሩ አጠቃላይ ኢንቨስትመንት በመደበኛ እና በካፒታል በጀት መልክ የሚያወጣው እያደገ የመጣ ሲሆን በዚህም መሰረት በ2002 ዓም ከነበረበት 331 ሚሊየን ብር በያዝነው የበጀት ዓመት ወደ 1.5 ቢሊየን ብር አድጓል ፡፡ይህም 5 እጥፍ እድገት ያመለክታል፡፡ 
ይህ የተከበረው ምክር ቤት የበጀት ዓመቱ ሲጀመር ባጸደቀው መሰረት ለካፒታል እና ለመደበኛ ስራዎች ማስፈጸሚያ ከአንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮንብር በላይ ተመድቧል ፡፡ እንዲሁም ከነዚህ የበጀት አቅም በተጨማሪ በቻናል አንድ ፕሮግራሞች; ከከተሞች መሠረተ ልማት (ULGDP) ;ለአቅም ግንባታ ፕሮግራም (PSCAP) ለሴፍትኔት ለትምህርት ጥራት ማሻሻያ በድምሩ ብር 30.9 ሚሊየን ለአስተዳደሩ አስፈፃሚ ተቋማት ገቢ ተደርጎ በተያዘላቸው መርሀግብር መሰረት ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ 
በውጪ አስተዳደር ረገድም የመደበኛ በጀት ሥራ ማስኬጃ ድልድልን ለከተማ ቀበሌ መስተዳድር ጽ/ቤቶች፣ ለጤና ጣቢያዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፤ በካቢኔ ውይይት በፀደቀ የድልድል ቀመር ሌሎች እንደ መኪና ጥገና፣ ጎማ፣ ነዳጅ፣ ግዢ ቴሌፎን እና መስተንግዶ አገልግሎት የመሳሰሉትን ወጪዎችን ደግሞ በካቢኔ በፀደቀ የአጠቃቀም ስታንዳርድ መመሪያ በቁጠባ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ 

የካፒታል በጀት አጠቃቀምን በተመለከተ፡-

በጀት አመቱ ከGTP ዕቅዳችን ስኬት አንፃር የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎቶች በማስቀደም የተለያዩ 111 አዲስና ነባር ፕሮጀክቶችን ታቅደው በመከናወን ላይ ይገኛሉ ፡፡በአፈጻጸም ደረጃም ባለፉት 6 ወራት 3 ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል፣ 47 ፕሮጀክቶች ከ30 እስከ 80 ፐርሰንት ትግበራ ላይ የሚገኙ፤32 ፕሮጀክቶች የጨረታ ቅድመ ዝግጅት ላይ የሚገኙ፤ ፣13 ፕሮጀክቶች የጨረታ ትንተና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ፤ 4 ፕሮጀክቶች በአግባቡ ወደ ትግበራ ያልገቡ ሲሆን በ6 ወር ለመጠቀም ከታቀደው 279.4 ሚሊየን ብር ውስጥ 38 ፐርሰንቱን ማለትም 106.8 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎ ጥቅም ላይ ውሏል ፡፡

በተጨማሪም የምእተ ዓመቱን የልማት ግቦች ለማሳካት በበጀት አመቱ 68 ፕሮጀክቶች ጸድቀው በመተግበር ላይ ይገኛሉ ፡፡በዚህም መሰረት 8 ፕሮጀክቶቸ ተጠናቀዋል፣ 15 ፕሮጀክቶች ከ30 እስከ 80 አፈጻጸም ትግበራ ላይ የሚገኙ ፣ 36 ፕሮጀክቶች የጨረታ ቅድመ ዝግጅት ላይ ናቸው፣ አራት ፕሮጀክቶች ጨረታ ላይ ናቸው፣ አንድ ፕሮጀክት የጨረታ ትንተና በመጠናቀቅ ላይ ነው፣ 3ፕሮጀክቶች በአግባቡ ወደ ትግበራ ያልገቡ ናቸው እንዲሁም 1 ፕሮጀክት እንዲታጠፍ ተደርጓል ፡፡ ለስራው ማስፈጸሚያ ለ6 ወራት 87 ሚለዮን ብር በሥራ ለማዋል ታቅዶ 20.09 ሚሊየን ብር ወደ ፈጻሚ ተቋማት ዝውውር የተደረገ በመሆኑ የፋይናንስ አፈጻጸም 23% ሆኗል፡፡
ከላይ የተጠቀሰውን የአስተዳደሩን ገቢና ወጪ አስተዳደር በሥርዓት ለመምራት ባለድርሻ አካላትን አቅም በተለያዩ ሥልጠናዎችን የመደገፍ፣ የልማት ዕቅዳችንን ተፈፃሚነት በመስክና በካቢኔ ደረጃ በመገምገም በሚሰጡ የማጠናከሪያ አቅጣጫዎች መሠረት እንዲመሩ የማድረግ፣ ከግዢና ኮንትራት ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶችን በቅርብ ክትትል ተፈፃሚ እንዲሆኑ ማስቻል፣ ከፌዴራል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በተናበበ መልኩ የሚካሄደውን GDP ቀጣይ ጥናትን ማካሄድና ፤የአስተዳደሩን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የሶስተኛው አመት አፈፃፀም ደረጃ ለካቢኔ ውይይት አዘጋጅቶ የማቅረብ ሥራዎች ተካሂደዋል፡፡ የአራተኛው አፈፃፀም ተዘጋጅቶ ተጠናቋል፡፡ የአራተኛው አፈፃፀምም ተዘጋጅቶ ተጠናቋል፡፡
የአካባቢ ልማትን በዘጠኙም ቀበሌ መስተዳድር ነዋሪዎችና መንግሥት በህብረተሰቡ የተመረጡ የአካባቢ ልማቶችን የማከናወን ልምድ ዳብሮ ከአስተዳደሩ ዘጠኙም የከተማ ቀበሌዎች የአካባቢ ልማት ማስፈፀሚያ ብር 5,040,460(ብርአምስት ሚሊዮን አርባ ሺ አራት መቶ ስልሳ ) ገቢ የህብረተሰብ ድርሻ ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 992,424 ገቢ ማድረግ የተቻለ ሲሆን የዕቅድ አፈጻጸሙም 19.7 በመቶ ሆኗል ፡፡ቀጣይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ስራም ነው፡፡ 

በንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ሲሆን ከስትራቴጂካዊ ግቦች አንፃር፡- 

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለገበያ የሚያቀርቧቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ያለችግር መገበያየት እንዲችሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግና የገበያ እድልን በማስፋት በጥራት፣ በዋጋና በጊዜ አቅርቦት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል በመንፈቅ አመቱ 1385 አባላት ያላቸው 170 ኢንተርፕራይዞች የብር 43.8 ሚሊየን የሃገር ውስጥ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዶ፤ 4167 አባላት ላላቸው 248 ኢንተርፕራይዞች የብር 38.3 ሚሊየን የገበያ ትስስር ለመፍጠር ተችሏል፡፡ የእቅድ አፈፃፀሙም 87.4% ሊሆን ችሏል፡፡ 
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አገልግሎት በማመቻቸት ያለባቸውን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ የቁጠባን ባህል እንዲያዳብሩ በማድረግ ማስቆጠብ እና የተሰጣቸውን ብድር የማስመለስ እቅድ ተይዞ በመንፈቅ ዓመቱ ለ2469 አንቀሳቃሾች ብር 30 ሚሊየን ብድር ለመስጠት ታቅዶ ለ1,770 አንቀሳቃሾች የብር 22 ሚሊየን ብድር ተስጥቷል፡፡ የእቅድ አፈፃፀሙም 73.3% ሆኗል፡፡ ከዚህም የሴቶች ተጠቃሚነት 67% ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር 12.5 ሚሊየን ማስቆጠብ የተቻለ ሲሆን ብር 20.4 ሚሊየን ከውዝፍና ከዘመኑ ብድር ለማስመለስ ተችሏል፡፡ 
ለኢንተርፕራይዞች የኦዲት ኢንስፔክሽንና ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ እና አመዘጋገብ ድጋፍ በማድረግ ስህተቶች እንዲታረሙ ፤የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ነፃ በሆነ መልኩ ስራዎች እንዲያከናወኑ ለማድረግ ታቅዶ ለ143ኢንስፔክሽን አገልግሎት፤ ለ55ኦዲት አገልግሎት፤ለ143ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ እና አመዘጋገብ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ከእቅዳቸው አንፃር የመቶኛ አፈጻጸማቸውም 63%፤ 53%፤ 62% ተከናውኗል፡፡
በመንፈቅ ዓመቱ በግል፣ በንግድ ማህበር እና በህብረት ስራ ማህበር 2500 ስራ ፈላጊዎችን በድምሩ በ720 ኢንተርፕራይዞች ለማደራጀት ታቅዶ፤2451 ስራ ፈላጊዎች በ1938 ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተዋል፡፡ ከፍተኛን ድርሻ የሚየዘው በግል የተደራጁት ናቸው፡፡ 
ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ የስልጠና፣ የቴክኖሎጂ፣ የንግድ ልማት፣ መረጃና የካይዘን ልማት ድጋፎች ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡ በግማሽ አመቱ 5,000 ነባርና አዲስ የኢንተርፕራይዝ አባላት በቴክኒክና ሙያ እና የንግድ ስራ አመራርስልጠና እንዲያገኙ ታስቢ ለ947 በቴክኒክ ሙያ እንዲሁም 3103 በንግድ ስራ አመራር በድምሩ 4050 ሰዎች ስልጠና አግኝተዋል፡፡ (ለ3,114 (62.3%) ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዝግጁ የሆኑና የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚካሄድባቸው 7 ፕሮቶታይፖች ዝግጁ ለማድረግ እቅድ ተይዞ በስድስት ወሩ ውስጥ 19 ፕሮቶታይፖች ተዘጋጅተዋል:: ለ17,000 አንቀሳቃሾች የመረጃና ምክር አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለ17,241 (101.4%) አንቀሳቃሾች የመረጃና ምክር አገልግሎት ተሰጥቷል፣ ለ60 ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የካይዘን ትግበራ ተጠቃሚ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸው ዘላቂ እንዲሆን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ታቅዶ በስድስት ወሩ 60 ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የካይዘን ትግበራ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
የመስተዳደሩ ነዋሪ እውቀቱን ጉልበቱን ችሎታው እና ገንዘቡን በማቀናጀት በፍላጐት ላይ የተመሰረተ የህብረት ስራ ማህበር እንዲደራጅና ግንዛቤን በመፍጠር እና በማሳደግ ፍላጐቱን መሠረት ባደረገ የሥራ ዘርፍ እንዲደራጅ እና እራሳቸውን እንዲጠቅሙ ለማድረግ 18 ማህበራት ለማደራጀት ታቅዶ 16 የተዳራጁ ሲሆን የመቶኛ አፈጻጸሙም 88% ነው፡-
ማህበራት በህብረት ስራ አዋጅ ደንብና መተዳደሪያ መሠረት እንዲሰሩና ሃብትና ንብረታቸው ሳይባክን ጤናማ የንብረት አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖቸው በማድረግ ውጤታማነታቸውን ለማስቀጠል እቅድ ተይዞ ለ33 ማህበራት የኦዲት ፤ለ103 ማህበራት የኢንስፔክሽን፤ ለ62 ማሀበራት ደግሞ ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ እና አመዘጋገብ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ የእቅድ አፈጻጸሙም ፡63%፤ 53% ፤ 62% ሆኗል የኢንዱስትሪ አቅምን በማሳደግ ረገድ ሥራ የጀመሩ የኢንዱሰትሪ ባለሃብቶችንና ተቀጣሪ ሠራኞችን የጥራቱ ስራ አመራር የቴክኖሎጂ ምርታማነት ማሻሻያ ስልጠና እና የመረጃና ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ 60 ታቅዶ 23 የተከናወነ ሲሆን አፈጻጸሙም 41% ሆኗል፡፡
የኢንዱስትሪ ልማት ማስፋፋት ረገድየኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን ምርታማነትን ሊያሣድጉ የሚያስችሉ መረጃዎችን መሰብሰብ ለመተንተን ጥናቶችን በማካሄድ ውጤቱን ለተጠቃሚ ባለሃብቶች በማድረስ ማምረትና ማቀነባበር የጀመሩ ኢንዱስትሪዎች ቁጥር 6 ታቅዶ 3 የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙም 50% ነው፡-
የባህል ኢንዱስትሪ በማስፋፋት ረገድ በአስተዳደሩ የሚገኙ የሥነ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ ዕድ-ጥበብ፣ ስራዎች ለማስፋፋት ውሰፊታዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ ሳይበረዙና ቅርፃቸውን ሳይለውጡ ለዘመናዊ የፈጠራ ሥራ በመሠረታዊነት እንዲያገለግሉ ለማድረግ በስድስቱ ወራት በተለያዩ ኪነጥበብ ዘርፍማለትም 47 በእደ ጥበብ ማህበራት ፤10በስነ-ጥበብ የተደራጁ አማተር ክበባት የተደራጁ ሲሆን የመቶኛ አፈፃፀማቸው 94% እና 111 % ሆኗል፡፡
ልማታዊ ባለሃብትን ቁጥር በመጨመር ረገድ የአስተዳደሩን ንጽጽራዊ ጠቀሜታ መሠረት ያደረገ የማስተዋወቅ ሥራ በተለያዩ የማስታወቂያ ዘዴዎች በመጠቀም የግል ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሣደግ ግብ ተይዞ፡- 80 አዲስ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ፤ በቁጥር 24፤ለውጥ/ምትክ ኢንቨስትመንት ፈቃድ፤ 55 የኢንቨስትመንት ፈቃድ እድሳት የተፈጸመ ሲሆን 107% 68% እና69% ተከናውኗል፡፡

በመንፈቅ አመቱ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ 80 ባለሃብቶች ያስመዘገቡት መነሻ ካፒታል ብር 914 496 814 ሲሆን ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው አገልግሎት ወይም ምርት ሲጀምሩ 3,432 ቋሚ እና 1,532,ጊዜያዊ በድምሩ 4,964 የሥራ እድል የሚፈጠር ይሆናሉ፡፡80 የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱት ባለሃብቶች ውስጥ 6 ሴቶች ሲሆኑ ያስመዘገቡትም ካፒታል መጠን 31,662,282 ነው፡፡
በግብርናው ዘርፍ በስድስቱ ወራት በተካሄደ እንቅስቃሴ በተፋሰስ ልማት በዝግጅት ምዕራፍ መከናወን ከሚገባው ጉዳዮች የእቅድ ዝግጅት ላይ 3ቱንም ክንፎች ከማወያየት አንፃር 56,851 ታቅዶ 36,470 (64 በመቶ) የህብረተሰቡን ክፍል ማወያየት ተችሏል፡፡ የግብዓት ዝግጅትም ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡ ፈፃሚውን ከማዘጋጀት አንፃር 111 አመራሮች፣ 376 የገጠር ባለሞያዎች 650 ቀያሾች 5,000 ሞዴል አርሶና አርብቶ አደሮች እና 35,000 መላው የአርሶ አርብቶ አደሮች ማሰልጠን ተችሏል፡፡ አደረጃጀትን ከማጠናከር አንፃር 38 ዩኒት ኤክስቴንሽን፣ 850 የልማት ቡድን እና 3,990 የ1ለ5 ኔትወርክ፣ በ15 ቀበሌዎች 127 የልማት ቡድን 570 የአንድ ለ1 ኔትወርክ፣ በመስኖ 881.5 ሄክታር በሰራዊት መልክ እየለማ ይገኛል፡፡ 780 የሴቶች ልማት ቡድን 3,730 የ1ለ5 አደረጃጀቶች ተፈትሸው ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ 
በግብርና ልማት ስራዎች ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል ሰፊ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በ2006 እና 2007 በገጠሩ ዝናብም መሰረት በማድረግ 14,450 ሄክታር መሬት በዋና ዋና ሰብሎች ለመሸፈን ታቅዶ 12,532 ሄክታር ሊዘራ ችሏል፡፡ ከዚህም በላይ 140,100 ኩንታል ምርት ተገኝቷል፡፡ በመስኖም 2,857 ሄክታር መሬት በማልማት 479,420 ኩንታል ምርት ተሰብስቧል፡፡ ባለፉት 6 ወራት በእንስሳት ሃብት ንዑስ ዘርፍ ከተካሄዱት እንቅስቃሴዎች ለ46,198 እንስሳት የህክምና አገልግሎት የተሠጠ ሲሆን፤ ለ218,122 እንስሳት ልዩ ልዩ ክትባቶች ተሰጥቷል፡፡ ከዚህ ውጪ የእንስሳት ህክምናና ክትባት ዘመቻ በማካሄድ ለ1977 እንስሳት የህክምና አገልግሎት እንዲሁም ለ121,664 እንስሳት የመከላከያ ክትባት መስጠት ተችሏል፡፡ 
በምርት ዘመኑ መጀመሪያ በተከሰተ የእርጥበት ማነስና የስርጭት ችግር ሳቢያ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ቀድሞ በመዳሰስ የእርጥበት ችግርን መቋቋም የሚችሉና ፈጥነው የሚደርሱ ዘሮችን በማሰራጨት አምራቹ ክፍል ችግሩን እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡ የእንስሳት የመኖ አቅርቦት ድጋፍም ተደረጓል፡፡ 
የገጠሩን የምርትና ምርታማነት ደረጃ ለማሻሻል በሚደረግ የግብአት አቅርቦት ስራ በስፋት ተከናውኗል፡፡ በዚህም መሠረት ለተደራጁ ወጣቶች የቀፎ አቅርቦት ድጋፍ የማድረግ፤ በችግኝ ጣቢያዎች ምርታማ የፍራፍሬ ችግኞችን የማዳቀል ስራን የማከናወን፣ የመኖ ማቀነባበሪያ እና የዶሮ ብዜት ማእከልን ይዘት የማሻሻል ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ 
የገጠሩን የመሬት የመጠቀም መብት ለማረጋገጥ በዘመኑ ግማሽ ዓመት 5ሺ ለሚደርሱ ባለይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ በተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎችም በአርሶና አርብቶ አደሩን አቅም ተፋሰስ ልማት የማጎልበት እና ለቀጣይ የተፋሰስ ልማት የሚውሉ ቦታዎችን የማዘጋጀት የዘርፉን ስራ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ጥናቶች እና የማንዋል ዝግጅቶችም ተከናውኗል፡፡ 
በከተማውም የእንስሳት እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች በጥራትና ደረጃ በማስጠበቅ ሰፋ ያለ እንቅስቃሴ ተካሄዷል፡፡ በዚህም መሠረት 12 ጊዜ የዳልጋ ከብት ቆዳ የጥራት ፍተሻ በማድረግ 11,545 ቆዳና 38,950 ሌጦ ደረጃ ወጥቶለት ለማዕከላዊ ገበያ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ 
የውሃ ሃብት ልማት ስራዎችን በተመለከተ በገጠሩ 5 የገጠር መጠጥ ውሃ እና 5 የመስኖ ግንባታ ስራዎች በዘመኑ የተጀመሩ ሲሆን በግንባታው ሂደትም ህብረተሰቡ በቀጥታ ተሳታፊ እየሆነ ባለፉት 6 ወራት 29 የውሃ ተቋማት ተጠግነው ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት የገቡ ሲሆን ሌሎች 12 የኤሌክትሮ መካኒካል ጥገና ተደርጎላቸው ወደ አገልግሎት ገብተዋል፡፡ በመስመር ጥገናም ተገቢውን ድጋፍ ተደርጎ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የውሃ ተቋማት የብልሽት መጠንን ከ5% ለማድረስ እየተደረገ ያለው ጥረት ስኬታማ እየሆነ ነው፡፡
ግዢው በማዕከል የተፈፀመው የውሃ መቆፈሪያ ሪግ እና ተዛማጅ መሳሪያዎች ርክክብ ተደርጓል፡፡ የዚህ የቁፋሮ ክፍል የሰው ሃይል እየተሟላ እና ተገቢው የአቅም ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን በቅርቡ ከኩባንያው ጋር በመሆኑ የሙከራ ቁፋሮ ይጀመራል፡፡ 
ለማዕድን አምራቾች 11 ፍቃድ በመስጠትና የ48 ፍቃድን በማደስ እስከ ብር 371,590 ገቢ በማሰባሰብ እንቅስቃሴ ተደርጓል፡፡ በኢነርጂ ዘርፍም በ12 ቦታዎች የሚገነባውን የባዮ ጋዝ ኢነርጂ የማስጀመር ስራ እየተከናወነ ሲሆን 3536 የተሻሻሉ ምድጃዎችም ለገጠሩ ተጠቃሚ ተሰራጭቷል፡፡ ለ111 ተጠቃሚዎች የቤተሰብ ሶላር ለማሰራጨት በታቀደው መሠረት የመረጣና የብድር ምችችት ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኒሎጂ ሰርቶ ማሳያ ማዕከልም ግንባታው እየተከናወነ ነው፡፡ 
የአደጋ ስጋት ቅነሳ እና የምግብ ዋሰትና ስራዎችን በተመለከተ የተሟላ የአደጋ ክስተት ክትትልና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ የአደጋ ክስተተን አስቀድ በመጠቆም ረገድ 97% ስኬታም ተግባር ተከናውኗል፡፡ ይህንም መሠረት በማድረግ ወቅታዊና ተገቢ ምለሽ መስጠት ከታቀደው 94% ለማሳካት ተችሏል፡፡ ለአደጋ ምላሽ የዝግጁነት አቅም በማሳደግ በኩል ተገቢውን የአቅርቦት ክምችት ዝግጁ በማድረግ ተገቢው አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡ 
የምግብ ዋስትናን በተመለከተ ዓመታዊ የምግብ ክፍተታቸውን ያሟሉ ቤተሰቦች ቁጥር ለማሳደግ በተጣለው ግብ አኳያ 36,882 ተጠቃሚዎችን በማህበረሰብ ስራ ለማሳተፍ ተችሏል፡፡ 12,253 ቀጥታ ተረጂዎችን ድጋፍ ያገኙ ሲሆን በጥቅሉ 49,136 ተጠቃሚዎችን ለመድረስ ተችሏል፡፡ 
ለ47,993 የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች 6 ጊዜ ድጋፍ በማድረግ፣ በ18 ቀበሌዎች የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ዳግም ልየታ በማሳደግ፣ ለ750 ተጠቃሚዎች ከግብርና ውጪ ገቢ የማስገኛ ስራ ላይ እና በኢንተርፕሪኒየር ሺፕ ስልጠና ድጋፍ በማድረግ እንቅስቃሴ ተደርጓል፡፡ 

በማህበራዊ አገልግሎት ረገድ የታቀዱ ስትራቴጂያዊ ግቦች ለማሳካት አፈጻጸም በተመለከተ፡-

ከጤና አገልግሎት የዓመቱ ትኩረት አቅጣጫዎች፡- አንዱ በሆነው የህብረተሰቡን የጤናውን የባለቤትነት ስሜት ማሻሻል ሲሆን ይህንን ስትራቴጂካዊ ግብ ለማሳካት በዘጠኙ የከተማና በ38ቱ የገጠር ቀበሌ መስተዳድራት የጤና ልማት ሠራዊት ትግበራን እስከ ማህበረሰብ በማውረድ እየተሠራ የሚገኝበት ደረጃ ማድረስ ተችሏል፡፡ 

የእናቶች ሞትን መቀነስና የምዕተዓመቱን ግብ ማሳካትን በተመለከተ ቅድመ ወሊድ፣ በመውለጃ ወቅትና የድህረ ወሊድ የጤና ክትትልና አገልግሎት አመላካቾችን መሠረት አድርጎ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ በተቀመጠው መሠረት በስድስት ወራት በሰለጠነ የጤና ባለሙያዎች ክህሎት የማዋለድ አገልግሎት ለ5384 ተገልጋይ ታቅዶ ለ4013 የተሰጠ ሲሆን የመቶኛ ዕቅድ አፈፃፀሙ 75% ሲሆን፣ የድህረ ወሊድ አገልግሎትም ለ5738 እናቶች ለመስጠት ታቀዶ ለ5239 አገልግሎት የተሰጠ አፈፃፀሙም 91% ነው፡፡ ለ6875 ነፍሰጡር እናቶች የቲቲ-2 ክትባት ለመሥጠት ታቅዶ 4340 በመከናወኑ የእቅድ አፈፃፀም ንፅፅሩ 63% ነው፡፡ለ8198 ነፍሰጡር እናቶች ስለ ኤች አይ ቪ ምክርና ምርመራ ተሰጥቷል የዕቅዱ አፈፃፀምም 121% ሆኗል፡፡
የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን የማሻሻል ስትራቴጂካዊ ግብንም ለማሳካት፣ ለ18742 እናቶችና ወጣቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ የዕቅድ አፈፃፀሙም 43% ነው፡፡
የህፃናት ሞትን መቀነስንና የተሸሻለ የህፃናት ጤንነት መፍጠርን በተመለከተ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ የህፃናት በሽታዎችን ለመከላከልና የህፃናት ጤናን በማሻሻል ረገድም ለ4212 ሀፃናት የሮታ ቫይረስ ሁለት ክትባት ተሰጥቷል፡፡ ለ4154 ህፃናት የፔንታቫላንት ሦስት ክትባት የታቀደውን 63% ተሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ለ3612 ህፃናት የኩፍኝ መከላከያ፣ ለ3516 ህፃናት የሁሉንም ክትባቶች እንደ ዕድሜያቸው እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ የዕቅዱ አፈፃፀም እንደቅደም ተከተላቸው 58% እና 56% ሆኗል፡፡
በተጨማሪም 363 ለሚሆኑ ሰዎች የቅድመ ፀረ ኤች አይቪ ህክምና ክትትል፣ የታቀደውን 91% አፈፃፀም ተከናውኗል፡፡ ፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት በመጠቀም ላይ የሚገኙ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች በቁጥር 5647 የተከናወነ የእቅድ አፈፃፀሙ 88% ሆኗል፡፡
ፀረ ኤች ኤይቪ መከላከያን የጀመሩ 8703 የእቅዱን 101%፣ የፀረ ኤች አይቪኤድስ የምክርና ምርመራ አገልግሎት መስጠት በቁጥር 42,305 ታቅዶ ለ55,125 ሰዎች አገልግሎት በመሰጠቱ 130% አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡
የቲቢ በሽታን የመከላከልና መቆጣጠር አገልግሎትን በተመለከተ በ6 ወሩ 534 ህመምተኞች ለመለየት ታቅዶ 829 ተለይተዋል፡፡ አፈፃፀሙም 155% ሲሆን፤ የስጋ ደዌ ህመምተኛ 6 ታቅዶ 9 ተለይቷል፡፡ የወባ በሽታን በመከታተልና መቆጣጠር ረገድ የኬሚካል ርጭት ሽፋን በቁጥር35505ታቅዶ 18,449 የተከናወነ ስለሆነ የእቅድ አፈፃፀሙ 52% ሆኗል፣የአጎበር ስርጭትን በተመለከተ በስድስቱ ወራት 73,500 የተከናወነ አፈጻጸሙም ከ100% በላይ ሆኗል፡፡ ለወባ በሽታ ምርመራ ህክምና የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በሁሉም ጤና ተቋማት የማድረስ የመከታተልና የመደገፍ ሥራዎች በእቅዳቸው መሠረት ተከናውነዋል፡፡ 
የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያ አቅርቦትና አሠራር የማሻሻል ዝርዝር ተግባራት 100% አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ አሰጣጥ ረገድ ከጤና ቢሮ እስከ ህብረተሰብ ድርስ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ የሚሰጥ ኮሚቴ በማቋቋም መረጃዎችን በማሰባሰብና በማጣራት ምላሽ የመስጠት ሥራ በተቀናጀ መልኩ ተመርቷል፡፡ በለውጥ ሥራዎችና ኮሚኒኬሽን ረገድ የጤና አገልግሎት በተመለከተ የማስተዋወቅና የግንዛቤ ማስያዝ ሥራ በሬዲዮ ቴሌቪዥን በጋዜጣ መግለጫዎች የመስጠት ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ 
የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልም በተለያዩ ፕሮግራሞች ለባሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ለማሻሻል የምግብና ጤና ነክ ተቋማት፣ በሱቅና በገበያ ማዕከላት የሚገኙ የምግብ ሸቀጦችን መቆጣጠር፣ ለጤና ባለሙያዎች አዲስ የሙያ ምዝገባና ፈቃድ ምሥክር ወረቀት የመስጠት ፤የግል የመድሃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች ቁጥጥር በታቀደው መሠረት ተከናውኗል፡፡
የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን በጤና ኬላዎች በስፋት የሚሰጥበት 31 ሲሆኑ የእቅድ አፈፃጸሙ 100% ሆኗል፡፡ በጤና ልማት የተደራጁ ሴቶች ብዛት 60,741 ሲሆኑ እነዚሁም 10,589 የ1ለ5 ጥምርታ መስርተዋል፡፡ በ1ለ5 ከተደራጁት ሴቶች 22,886ቱ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል፡፡
የትምህርት ዘርፍ አፈጻጸም በተመለከተም፤ ለድሬዳዋ መስተዳድር ትምህርት በጥራት፤ በብቃትና ፍትሃዊነት በመስጠት በማህበራዊና ፖለቲካዊ አገልግሎት ዘርፎች ግብዓት የሚሆን ተገቢውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት የተጎናፀፈ የሰው ኃይል ለማፍራትና በሀገራዊው የዘላቂ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት የሚሳተፍ ብቁ ዜጋ የማፍራት ዓላማን ለማሳካት በ6 ወራት በተደረገ እንቅሰቃሴ፤
የትምህርት ሽፋንን ማሳደግ በተመለከተ የ1ኛ ክፍል ንጥር ቅበላ ምጣኔን በ2006 ማድረስ ከተቻለበት 69.7 ወደ 100%፣ ከ1-4ኛ ክፍል ከነበረበት 76.9% ወደ 100% ለማድረስ፣ ከ5-8ኛ ክፍልን በ2006 ከነበረበት 42.9 ወደ 90.8%፣ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍልና ከነበረበት 71.4 ወደ 95.10 ለማድረስ የ2007 የመጀመሪያው ስድስት ወር የተቀመጡ እቅዶች ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል፡፡
የትምህርት ጥራትን በተመለከተ ለደረጃ ብቁ የሆኑ መምህራንን የተማሪ መምህራንን ጥምርታ እና የተማሪ ክፍል ጥምርታ በ2006 ከነበረበት 10ኛ ድርሻ ወደ 2007 ጥቅል ድርሻ ለማድረስ የታቀዱ ዝርዝር ተግባራት በእቅዳቸው መሠረት ተከናውኗል፡፡
የትምህርት ፍትሃዊነትን በተመለከተ የፆታ ምጥጥን በየክፍል ደረጃዎቹ ካለበት 0.80 ወደ 1 አፈፃፀም ደረጃ ለማድረስ የታቀዱ ተግባራት በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡
የትምህርት ብቃትን በተመለከተ፤ መጠነ መቋረጥን በ1ኛ ክፍል ከ19.8 ወደ 0.5፤ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ከ6.4 ወደ 0.5፤ መጠነ መድገም ከ4ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በ2006 ከነበረበት 10.6 ወደ 0.5 ለማድረስ የታቀዱ ዝርዝር ተግባራት በእቅዳቸው መሰረት ተከናውኗል፡፡
በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበር ላይ ፈፃሚዎችንና አሰልጣኞችን ማብቃት የእቅዱን 95.9% ተከናውኗል፡፡ ከቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ተቋማት በመደበኛና በአጫጭር ስልጠና የሰለጠኑ ሳይበታተኑ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ ማስቻል የእቅዱን 97% ተከናውኗል፡፡
ከኢንተርፕሩነር ሺፕ ልማት ጋር በመተባበር በከፍተኛዎቹ ኢንተርፕሩነር ሺፕ የበቁ አስልጣኞችን በመጠቀም ሌሎች ቀሪ አሰልጣችን የማፍራት ስራ የታቀደውን 89.6 % ተከናውኗል፡፡

በኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት፡-

በመሠረተ ልማት ማስፋፋት የኣምስቱ ዓመታት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን መሠረት አድርጎ በተካሄደ እንቅስቃሴ፣ በ2007 የበጀት አመት ከክልሉ መንግስት በተመደበ የብር 3,966,667 ማቺንግ ፈንድና በአለም ባንክ ድጋፍ ሳቢያን በጎሮ ወንዝ ላይ ከመንገድ በላይ ለመገንባት የታቀደው የ0.7 ኪሎ ሜትር የጎርፍ መከላከያ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሰነዱ ተጠናቆ ጨረታው በአየር ላይ ውሏል፡፡በዚሁ መሰረት የፕሮጀክቱ የ6 ወር አፈፃፀም 83.3% ሲሆን ፕሮጀክቱ ከኣመቱ የእቅድ አፈፃፀሙ ደግሞ 25% ላይ ይገኛል፡፡
የፍሳሽ ማስወገጃ ድሬይኔኤጅ ግንባታ ስራ በአለም ባንክ ድጋፍ በአማካሪ ለማስጠናት ዝክረ ተግባሩ ተዘጋጅቶ ከከተማ ፕላን አንጻር ተተችቶ በጥር ወር ጨረታ እንዲወጣ ተዘጋጅቶ የሚገን ሆኗል፡፡ 
የመንገድ መብራት ዝርጋታ በ2007 የበጀት አመት ከክልሉ መንግስት በተመደበ ብር ሶስት ሚሊዮን ሀምሳ ስድስት ሺ ማቺንግ ፈንድና በአለም ባንክ ድጋፍ በከተማው ውስጥ አዲስ ለመዘርጋት የታቀደው የመንገድ መብራት የጨረታ ሰነድ ዝግጅት ተጠናቆ ጨረታው በአየር ውሏል ፡፡ የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም 83.3በመቶ ሆኗል፡፡ 
የሀፍካት ድልድይ ግንባታ ነባር ፕሮጀክትን በተመለከተ የመሰረት ስራው(Sub-Structure Work) 75% ድርሻ 100% የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የተሸካሚውን ክፍል ስራ (Super Stucture ) ከተያዘው የግንባታ ድርሻ 25 ፐርሰንት የተከናወነው 13% ነው፡፡ በዚህም መሰረት የዚህ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀምም 88% ተጠናቋል፡፡ 
የገጠር መንገድ ግንባታ በተመለከተ የ42 ነባር የገጠር መንገድ ግንባታ ባለፈው ስድስቱ ወራት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል፡፡ የ60 ኪሎ ሜትር አዲስ የገጠር መንገድ ግንባታ በ9 ቀበሌዎች የሚካሄድ 46 ኪሎ ሜትር ጠቅላላ የሰርቨይንግ ፤የዲዛይንና የጨረታ ሰነዱን አጠናቆ የመንገድ ስራውን ለኮንትራክተሮቹ ለማስረከብ ዝግጅቱን 100% ተጠናቋል ፡፡
የመንገድ ጥገናዎች በሮድ ፈንድ በስድስቱ ወራት7.5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጠጠር ማልበስ ጥገና፤ የ134 ሜትር ኩብ የአስፋልት መንገድ ፓችንግ ጥገና ስራ፤የ303 ሜትር ኩብ የአስፋልት ኦቨር ሌይ ጥገና ስራ፤የ1968.7 ካሬ/ሜትር የኮብል ስቶን መንገድ ጥገናና የ1204 ሜትር ኩብ የዜብራ ቅብ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
የ5 ኪ/ሜ አዲስ ኮንክሪት ስፋልት ግንባታ በ03 ቀበሌ ከሽኔሌ የክርስቲያን መቃብር እስከ ድሬዳዋ ፖሊስ መምሪያ ዋና አስፋልት ድረስ የ2.7 ኪ/ሜት እንዲሁም በሳቢያን ጀርባ ሠፈር የሚገነባው 2.3 ኪ/ሜት የሰርቬይንግ፣ የዲዛይንና የጨረታ ሰነድ ዝግጅት በአማካሪው ድርጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በእቅዱ መሠረት አፈፃፀሙ 15% ላይ ይገኛል፡፡
የ10.28 ኪ/ሜትር የኮብል ስቶን የመንገድ ሥራ ከአስተዳደሩ በተመደበ 7.9 ሚሊዮን ማቺንግ ፈንድና በአለም ባንክ ድጋፍ በከተማው ውስጥ በተመረጡ 31 የተለያዩ ቦታዎች ለማከናወን የጠረጋና የሰብ ቤዝ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፤ በዚህም መሠረት የ6 ወራት አፈፃፀሙ 60% ሆኗል፡፡ 
በ2007 የበጀት በአስተዳደሩ በተመደበ የብር 2,716,866.67 ማቺንግ ፈንድና በአለም ባንክ ድጋፍ በከተማው ውስጥ ለመዘርጋት የታቀደው አዲሰ የ5 ኪ.ሜትር የጠጠር መንገድ ስራ ፕሮጀክት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ የዲዛይን የጨረታና ስፔስፊኬሽን ሰነድ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡በዚሁ መሰረት የፕሮጀክቱ የ6 ወር አፈፃፀሙ 60% ሲሆን የፕሮጀክቱ ከዓመቱ የእቅድ አፈፃፀሙ ደግሞ 18% ላይ ይገኛል፡፡
በ2007 በአስተዳደሩ በተመደበ የ2,000,000 ብር የመደበኛ ካፒታል ወጪ ለመጠገን የታቀደው የመንገድ መብራት ጥገና ስራ ፕሮጀክትን በተመለከተ ዋናው ስራ ለጥገናው የሚያስፈልጉትን የመለዋወጫ እቃዎችን ግዥ መፈፀም ሲሆን የስፔሲፊኬሽንና የጨረታ ሰነድ ዝግጅት ተጠናቆና በጨረታ ወጥቶ በጨረታ ትንተናና ግምገማ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት የፕሮጀክቱ የ6 ወር አፈፃፀሙ 100% ሲሆን አጠቃላይ ፕሮጀክቱ ከዓመቱ የእቅድ አፈፃፀሙ ደግሞ 40% ላይ ይገኛል፡፡
የ5,500 ሜ.ኩብ የገጠር መንገድ የጐርፍ መከላከያ ቼክዳም ግንባታ አዲስ ኘሮጀክትን በተመለከተ፡-ለግንባታው የሚያስፈልገው ጋቢዎን ግዥ የጨረታ ሰነድ ተዘጋጅቶና ጨረታው ወጥቶ በአሁኑ ግዜ የጨረታው ሒደት ተጠናቆ የጋቢዎን ርክክብ ተከናውናል፡፡በዚሁ መሰረት የፕሮጀክቱ የ6 ወር አፈፃፀሙ 100% ሲሆን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ የ2007 የእቅድ አፈፃፀሙ ደግሞ 50% ላይ ይገኛል፡፡
የመጠጥ ውሃ አገልግሎትን በተመለከተ፤ በአምስቱ አመታት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሠረት የንፁኅ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በ2007 ዓ/ም 100% ለማድረስ የታቀደ ሲሆን ይህንኑ ግብ ለማሳካት ከአስተዳደሩ በ2007 ዓ/ም 100 ሚሊዩን ብር ማቺንግ ፈንድ ተመድቦና ከአለም ባንክ የተገኘውን ብድር በማቀናጀት በውሃ ፕሮጀክት ማሻሻያ እንቅስቃሴ ተጀምሮ በጨረታ አሸናፊ በሆነው የቻይና ካምፓኒ 12 አዲስ ጉድጓዶች ቁፋሮ የዘጠኙ እየተካሄደ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪው በቁፋሮ ላይ ነው፡፡
በፕሮጀክቱ የኢንቨይሮመንት፤ የሶሻል ኢምፓክት አሰስመንት ጥናት በፕሮጀክቱ የሚፈናቀሉ ግለሰቦች ካሣ ለመክፈል የሚያስችል ሥራ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆኑ መረጃ የማጠናከር ሥራ እየተሠራ ይገኛል፡፡

የሲቪክ ስራዎችን በተመለከተ፡-

በሁለት ተከፍሎ የሪዘርቫየሮችና ሌሎች ግንባታዎችን የሚያከናወን ድርጅት ከመስከረም ወር ጀምሮ ሥራው በመቀጠል ከፍተኛ ይዘት ያላቸው በ4000 ሜ/ኩ ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው ሪዘርቫየሮች በፖሊስ መሬት፤ በጎሮ እና ገንደቦዬ እንዲሁም ባለ1000 ሜ/ኩ በእንጦጦ አካባቢ የፋውንዴሽን ሥራው ተጀምሯል፡፡ሁለተኛውና የቧንቧ መዘርጋት ሥራው የቧንቧው ግዢ በመዘግየቱ ምክንያት አቅርቦቱን እየጠበቀ የሚገኝ ሆኗል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ሥራዎች ምንም የማራዘሚያ ጊዜ የማይጠየቅበት በቀጣዩ በ2015 መጨረሻ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ 
በመደበኛ የውሃ አቅርቦት በስድስት ወራት 3.6 ሚሊየን ሜትር ኩብ የውሃ ምርት ለማምረት ታቅዶ 2.9 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የተመረተ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 82% ለተጠቃሚ ተሰራጭቷል፡፡
የፍሳሽ ማንሳትን አገልግሎት በተመለከተ፤ 15,645 ሜ/ኩብ ፍሳሽ ለማሰስወገድ ታቅዶ 13,760 ሜ/ኩብ የፍሳሽ ቆሻሻ የታቀደውን 85 % ተከናውኗል፡፡ የመኖሪያ ቤት ልማትና የመንግስት ህንፃዎች ኮንስትራክሽን ፕሮግራም ኤጀንሲ(የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት) የቤት ማስተላለፍና የፋይናንስ ሥራ ማጠናከር በተመለከተ ከቦንድ ሽያጭ ተመላሽ ከታቀደው ብር 22 ሚሊዮን 26 ሚሊየን የታቀደውን 118.2 ማስፈፀም ተችሏል፡፡
የቤት ማስተላለፍና ማስተዳደርን በተመለከተ እጣ የወጣላቸው የቤት እድለኞች ክፍያውን መክፈል የሚችሉ የቅድሚያ ክፍያ እንዲፈፅሙና የሽያጭ ውል ስምምነት እንዲያደርጉ ለ20 እድለኞች ታቅዶ 27 እድለኞች የውል ስምምነቱን ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈፅሙ ተደርጓል፡፡ አፈፃፀሙ 135% ሆኗል፡፡ የጽዳትና ውበት ኤጀንሲ በተመለከተ ከ2007 ዓ/ም 18,000 ኪሎሜትር የአስፋልትና ኮብል ስቶን መንገዶችን በፅዳት ለመሸፈን የታቀደው ስራ 85% ተከናውኗል፡፡ የቤት ለቤት ቁሻሻን በማህበራት ማሰባሰብ ሥራን 39,499 ሜ/ኩብ የታቀደውን 58% ተከናውኗል፡፡ 
በተመለከተ በዩ ኤል- ጂ-ዲ-ፒ ፕሮጀክት፡- የገንደ ቆሬ ሴፕቲክ ታንክ ግንባታ ፕሮጀክት፡- የጨረታ ስፔሲፊኬሽን ተዘጋጅቶ ጨረታ የወጣ ሲሆን የስድስት ወር እቅዱ 27% ውስጥ 15% ተከናውኗል በዚህ መሰረት አፈጻፀሙ 55.6% ላይ ይገኛል፡፡ የተሸከርካሪዎችና የመሳሪያዎች የግዥ ፕሮጀክቶች ፡- የ2 ሳይድ ሎደሮች፣የአንድ ዳምፐር፣የአንድ ገልባጭ ዳምትራክ፣የ40 የቆሻሻ ማሰባሰቢያ ጋሪዎች፣የ500 የእጅ መሳሪያዎችና የ200 የእጅ ጋሪዎች ግዥ ሁሉም የጨረታ ስፔሲፊኬሽን ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን የስድስት ወር እቅዱ 27% ውስጥ 10% ተከናውኗል፡፡ በዚህ መሰረት አፈጻፀሙ 37% ላይ ይገኛል፡፡ በአረንጓዴ ልማት ፓርክና መናፈሻ ሥራዎችን በተመለከተ ከከተሞች ፎረም ጋር በተያያዘ 15 ሄክታር ስፋት ያለው ፓርክ የተሟላ የእግረኛና የመኪና መንገድ ያለው 13.3 ሄክታሩ በአረንጓዴ ልማት የለማ ዘመናዊ ፓርክ ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡ ነባር ፕሮጀክቶች አፈፃፀም በተመለከተ፡- የለገሐሬ መስመር የመንገድ አካፋይ ከርብስቶን ግንባታ ፕሮጀክት ሥራው 100% ተጠናቋል፡፡

አዲስ የ2007 ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በተመለከተ፡-

ከቴሌ እስከ ሳቢያን አስፋልት መጨረሻ ያለው የ3,000 ሜትር የመሀል መንገድ አካፋይ ግንባታ ፕሮጀክት ስራው ተጠናቅቆ ርክክብ የተከናወነና በመቶኛ 100%ተከናውኗል፡፡ ከቬራ-ማረሚያ መስመር ያለው የመሀል መንገድ አካፋይ ግንባታ ፕሮጀክት ስራው ተጠናቅቆ ርክክብ የተከናወነና በመቶኛ 100%ተከናውኗል፡፡ከብሪጅ ካፌ እስከ ሰዒዶ ያለው የመሀል መንገድ አካፋይ ግንባታ ፕሮጀክት ስራው ተጠናቅቆ ርክክብ የተከናወነና በመቶኛ 100%ተከናውኗል፡፡ በህገ ወጥ የሰው እና የቤት እንስሳት በአረንጓዴ እፅዋቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት በመከላከል ረገድ በተደረገው ቁጥጥር በ6 ወር 1300 ብር የቅጣት ገቢ ተሰብስቧል፡፡ ሌሎች በፓርክና በመንገድ ዳር የጥላና የጌጣጌጥ ተከላ ተካሂዷል፡፡
በቄራ አገልግሎት በመደበኛና በልዩ ዕርድ በጠቅላላው 32885 እንስሳት ታቅዶ 24448 መቶኛ አፈጻጸሙም 74.3% ዕርድ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ 11,165 ቆዳ ለመሀል አገር ገበያ ተዘጋጅቷል፡፡ የእቅድ አፈፃፀሙም 78.6% ሆኗል፡፡ ከዕርድ አገልግሎት ክፍያ ብር2.1 ሚሊዮን፤ከተረፈ ምርት ዝግጅት ብር 233 ሺ በአጠቃላይ ብር2.34 ሚሊዮን የታቀደውን 64.67% ገቢ ተሰብስቧል፡፡ የአዲሱ ቄራ ግንባታ የነበሩበትን ውስብስብ ችግሮች በመፍታት ለቢሮ አገልግሎት፤የከብቶች ማረጃ ክፍሎች፤ የሀይድ ሼዶች ካፍቴሪያና የአጥር ግንባታው ተጀምሮ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡ የአዲሱ ቄራ የኤሌክትሮ መካኒካሉና የሳይት ወርኩ ስራ የጨረታ ዶክመንት ተዘጋጅቶለት ጨረታው በአየር ላይ ውሏል፡፡ 
በሌላ በኩል ህገወጥ ንግድ፤ህገወጥ እርድ፤ህገወጥ የመኪና ፓርኪንግና ህገወጥ የእንስሳት በአስፋልት መንገድ ዝውውር ፤ ደረቅ ቆሻሻ በየቦታው እንዳይጣል በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የሳኒቴሽን የቁጥጥር ስራዎች የታቀደውን ሙሉ በሙሉ ተከናውነዋል፤ በተጨማሪም 120 ህገ ወጥ ግንባታዎችን ለማፍረስ ታቅዶ 80 ህገ-ወጥ ግንቡታዎችን የማፍረስ ስራ ተሰርቷል፡፡ 
የክብር መዝገብ አገለ፤ግሎት በተመለከተ 1038 ደንበኞችን ለማስተናገድ ታቅዶ 764 ደንበኞች የተሰተናገዱ ሲሆን አፈፃፀሙ 74 ፐርሰንት ሲሆን ከአገልግሎት ክፍያ ብር 116,890 በእቅድ ተይዞ ብር 92,580 ገቢ ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ አፈፃፀሙ 79% ለመስሰብ ተችሏል፡፡
በከተማ አውቶቡስ ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት ለ252,000 ለሚሆኑ ሰዎች የአውቶብስ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 194,441 ተገልጋይ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ከዚሁ ገቢ ብር 306,000 ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 234,896 ተሰብስቦ ገቢ ተደርጓል፡፡ አፈፃፀሙም እንደ ቅድመ ተከተሉ 71.15% እና 76.76% ነው፡፡ 
የድሬዳዋ ከተማን የመሬት ዝግጅትና አሠጣጥ ሥርዓት በሀገሪቱ የመሬት አሰጣጥና አጠቃቀም ፖሊሲና ስትራቴጂ መሠረት በመምራት፣ የሚገነቡ ህንፃዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ ይዞታን ቀልጣፋና ዘመናዊ በሆነ መልኩ በማስተዳደር ረገድ በስድስት ወራቱ፤የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማሳደግ አንጻር 30 አዲስ ካርታ ለመስጠት ታቅዶ 43 ካርታ ተሰጥቷል፡፡ የስም ዝውውር አገልግሎት የተሰጣቸዉ ደንበኞች (በሽያጭ፣በስጦታና በፍ/ቤት ትዕዛዝ) ለአራት መቶ ሃምሳ ደንበኞች ለመስጠት ታቅዶ አራት መቶ ሰባ ስምንት ደንበኞች አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡በደንብ ቁጥር 24/98 መሰረት 1800 ማህደር ተለይቶና ተጣርቶ ለመመዝገብ ታቅዶ 1000 ፋይል ስራ ተሰርቷል፡፡ የይዞታ ማረጋገጫ ያልወሰዱትን መለየት እና ካርታ መስጠት 300 ታቅዶ 1340 ካርታ የማስረከብ ስራ ተሰርቷል፡፡ ካርታ ተዘጋጅቶላቸው ቅሬታ የቀረበባቸውን ለይቶ የህግ አግባብነታቸውን አጣርቶ ውሳኔ ለመስጠት 150 ታቅዶ 40 ቅሬታቸዉ ተፈቷል፡፡የካሳ ግምት ለሚጠይቁ 60 ደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ በተገልጋይ ጥያቄ መሠረት 48 ተከናዉኗል፡፡ በተጨማሪም ለስም ዝዉዉር፣ የይካፈልልኝ፣ የይካተትልኝ የጠፋ ካርታ መተኪያ ይሰጠኝ እና የውርስ ጥያቄዎች የግምት አገልግሎት ለሚጠይቁ 360 ደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 241 ተከናዉኗል፡፡ለፍርድ አካላት የንብረት ግምት አገልግሎት 30 ለመስጠት ታቅዶ ከዕቅድ በላይ 34 ተከናዉኗል እንዲሁም ለግብር የግምት አገልግሎት 450 ታቅዶ 164 ተከናዉኗል፡፡ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርአትን ከማሻሻል አንጻር ኮንዶሚኒየም ምዝገባና አስተዳደር አልግሎት ዙሪያ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችን ማስረጃ ለመስጠት 198 ታቅዶ 47 ተከናዉኗል፡፡በነባሩ ሬጉራላይዜሽን ከዚህ በፊት ሽንሸና ያልተካሄደባቸዉ አካባቢዎች ያሉትን ቅሬታዎች ለመፍታት ከሰነድ አልባ ንኡስ ፐሮጅክት ጋር በመሆን በተለያዩ ቀበሌዎች ማለትም በቀበሌ 02፡ ሳቢያን በብሎክ 105 አና የተለያዩ ብሎኮች ላይ አንዲሁም በጎሮ በተለይ በብሎክ 143 ፣157 አና ሌሎችም ብሎኮች ላይ ያሉ ችግሮችን በመዘዋወር የሳይት ጉብኝቶች ከማድረግም በላይ በቅርበት ከህብረተሰቡ ጋር በመገናኘት ዉይይት ተደርጓል፡፡ በቀጣይ በህብረተሰቡና ከሰነድ አልባ ንኡስ ፐሮጅክት መረጃዎች ከቀበሌ ጋር መረጃ በሟማላት መፍትሄ የሚሰጥበት ሁኔታ እየተመቻቸ ይገኛል፡፡በተመሳሳይ መልኩ በቀበሌ 03 ዲፖ አካባቢ በብልክ 135 አንዲሁም ከምድር ባቡር ጋር በተገናኘ የመዉጫ መግቢያ ችግር ያለባቸዉን በርካታ ነዋሪዎች መፍትሄ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡በዚህ በጀትዓመት ከተያዘው የነባር ሬጉላራይዜሽን ውዝፍ ካርታዎች ወደ 5064 የሚሆኑትን በመልካም አስተዳደር እቅድ በሶስት ወራት ውስጥ ለመስጠትና ከውዝፍንታቸው ለማውጣት ታቅዶ ባለፉት ወራት ወደ 3110 የሚሆኑት የተሰጠ ሲሆን ቀሪ ካርታዎች ያልተጠናቀቁት አመራሮችና ፈጻሚዎች ለተለያዩ የአስተዳደሩና የፌዴራል ስልጠናዎች ላይ በመሳተፋቸው ምክንያት ስለሆነ በቀጣይ የሚጠናቀቁ ይሆናል፡፡

የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥርን በተመለከተ፡-

የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ከማሳደግ አንጻር በከተማዋ ክልል ዉስጥ የሚተከሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች የሚመለከታቸዉ አካላት በማሳተፍ ፈቃድ መስጠት ስራ የአሰራር ማሻሻያ በማድረግ 30 ፍቃዶችን ለመስጠት ታቅዶ 18 ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡በህንፃ አዋጁ መሰረት በከተማችን የሚገነቡ የደረጃ ለ እና ሐ ሕንፃዎች በሙሉ የመጠቀሚያ ፈቃድ እንዲያገኙ ለማድረግ በመጀመሪያዉ ስድስት ወር 10 ፍቃዶች ለመስጠት ታቅዶ 8 ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡ በከተማዋ መዋቅራዊና አካባቢ ልማት ፕላን መሰረት ለ900 ባለይዞታዎች የፕላን ስምምነት ለመስጠት ታቅዶ 797 እንዲሁም በተሰጠዉ ፕላን ስምምነት መሰረት 900 ግንባታ ፍቃድ ለመስጠት ታቅዶ 784 ተሰጥቷል፡፡የክትትል ፣ ግምገማና ቁጥጥር ስርአት ከማሻሻል አንጻር በስታንዳርዱ መሰረት ግንባታው መካሄድ አለመካሄድ በ600 ፍቃዶች ላይ ክትትል ለማድረግ ታቅዶ 391 ፍቃዶች ላይ ክትትል ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ከተፈቀደው ግንባታ ፈቃድና የግንባታ ስታንዳርድ ውጪ ሆነው የተገኙ ግንባታዎችን በተፈቀደው መሰረት እንዲገነቡ ድጋፍ ማድረግ እና ከፍቃድ ውጪ በሚገነቡ ግንባታዎች ላይ እስከ ማስፈረስ የሚያደርስ እርምጃ ተወስዷል፡፡
መሬት ልማት፣ ባንክና ከተማ ማደስን የመሬት ዝግጅትና ባንክ ስርአትን ለማሻሻል አንጻር በLDP ጥናት መሰረት የቦታ አጠቃቀም (Land use) የቅየሳ፣የቦታ ሽንሽና እና ድንጋይ ተካላ ስራዎችን በከዚራ መልሶ ማልማት የተዘጋዉ 0.78 ሄክታር መሬት ላይ ተሰርቷል፡፡ በተጨማሪም ቦታዉን በመሬት ባንክ የመመዝገብ ስራና በግልጽ ጨረታ በመሸጥ 17 ሚሊዮን ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ከይዞታ አስተዳደር ዉጪ የሚገኙ ቦታዎችን፣ በእንዱስትሪ ዞን እና በከተማ ዉስጥ ለተለያየ አገልግሎት ለማልማት ወስደዉ አለማልማታቸዉ የተረጋገጠ አልሚዎች ተለይቶ በመመዝገብ 15 ሄክታር መሬት ለማስመለስ ታቅዶ 7.27 ሄክታር መሬት የማስመለስ ስራ ተሰርቷል፡፡የለማ መሬት እና ለአልሚዎች ተሰይቶ ሳይለማ የቀረ መሬት ተመላሽ በማድረግ መሬቱን ከህገ-ወጥ በመከላከል 36.78 ሄክታር ጥበቃ ለማድረግ ታቅዶ 8.05 ሄክታሩ የጥበቃ ስራ ተሰርቶለታል፡፡አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ከማሳደግ አንጻር ለማንፋክቸሪንግ፣ ለከተማ ግብርና፣ ለአነስተኛና ጥቃቅን፣ ከጨረታ ዉጪ (በምደባ) 6 ሄክታር መሬት ለማስተላለፍ ታቅዶ 31.6 ሄክታር መሬት ተላልፋል፡በሳቢያን መልሶ ማልማት 2.14 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን ከዚህ አካባቢለሚነሱ በቀበሌ ቤት ለሚኖሩ 6 አባዎራዎችን የኮንደሚኒየም ቤት እንዲያገኙ ተደርጓል ፡፡ 75 የግል ይዞታ ላላቸው አባወራዎች የመኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታ የተዘጋጀ ሲሆን የካሳ ክፍያውን በማስከፈል ቦታውን ሙሉ በሙሉ ነፃ ተደርጎ ለመሸንሸን ሥራዎች በቀሪ ጊዜ የሚከናወን ሆኗል፡፡
ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርአትን ከማሻሻል አንጻር የጥናት ሰነዶች፣ የህግ ማዕቀፎችና የተለያዩ መረጃዎችን የማደራጀት ስራ ተሰርቷል፡፡ በተቋሙ በዘመናዊ የመረጃ አያያዝና እና የመረጃ ልውውጡን የተሳለጠ ማደረግና የባለድርሻ አካላት ተደራሽ ማደረግ፡፡ነባሩ CIS ያለበትን ክፍተት ለመለየት የዳሳሳ ጥናት ተካሂዷል፡፡ እንዲሁም ከINTAPS ጋር ግንኙነት በመፍጥር ሲስተሙ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ በብር 380,000 ስምምነት ዉል ተፈጽሟል፡፡ሲስተሙ የሚሰራዉ በሞጁላር ሲስተም ሲሆን በአጠቃላይ ዘጠኝ ሞጁል ይኖረዋል፡፡ እስከ አሁን ሁለት ሞጅሎች ተጠናቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ህዝባዊ መሰረት ያለው ስፖርት እንዲስፋፋ፣ ህብረተሰቡን የስፖርት ተሳትፎ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ውጤታማ ስፖርተኞችን የማፍራት ተልዕኮን ለማሳካት በዓመቱ በተደረገ እንቅስቃሴ፤ የስፖርት አደረጃጀቶችን በተመለከተ በ6 ወራት ውስጥ 30 ስፖርት ማህበራትን በሰው ኃይል የማጠናከር ሥራ በከተማና በገጠር በ7 የስፖርት ዓይነቶች ለሴቶች ስፖርት ውድድር ዝግጅት በቀበሌ ደረጃና በድርጅቶች 60 ቡድኖች ሲፈጠሩ ለ32 የስፖርት ቡድኖችና የስፖርት ማህበራት የስፖርት ማቴሪያሎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የህብረተሰቡን የስፖርት ተሳትፎን በተመለከተ በስፖርት ለሁሉም በ6ወራቱ 82,840 አሳታፊዎች በስፖርት ለሁሉም ፕሮግራም ላይ ተሳትፈዋል፤ በልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮችም 5770 ተሳትፈዋል፤ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም 120,000 ተመልካች በመላው ድሬዳዋ የሴቶች ሰፖርት ጨዋታ በብስክሌት ውድድር፣ በቅርጫት ኳስ በተመልካችነት ተሳትፈዋል፡፡ ገቢ ማሳደግን በተመለከተ በአስተዳደሩ የሚካሄዱ የስፖርት ፌስቲቫሎች በ6ቱ ወር 214,488 ብር ገቢ ለማሰባሰብ ተችሏል፡፡ አፈፃፀሙም ከታቀደው 100% በላይ ሆኗል፡፡
የስፖርት ማበልፀጊያ በተመለከተ ነባሩ የኳስ ሜዳ የሳር ተከላ፣ የክቡር ትሪቡን መቀመጫዎች እድሳት እና የሩጫ ትራኩን የማዘጋጀት ሥራበእቅዱ መሰረት በጥራት ተከናውኗል፡፡

በፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳይ ዘርፍ፡-

የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የህዝብና የመንግስት ጥቅምን በማስከበር የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ፍትህን በማስፈን ረገድ፣ የአሰተዳደሩን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግና ለልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የአስተዳደሩ አብይ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አባላት ከሆኑት ከፌደራል የፀጥታ ሃይሎች፣ ከአጎራባች ፀጥታ ሀይሎች ዞኖችና ወረዳዎች ጋር በስድስቱ ወራት 6 የግንኙነት መድረክ ፈጥሮ ለመስራት ታቅዶ አፈፃፀሙ 100% ሆኗል፡፡ 
የህዝብና የመንግሥት ተቋማትን የህዝብ ማዘውተሪያ ስፍራዎችንና የስጋት ቀጠናዎችን በመለየት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ሥራ በዕቅዱ መሠረት ተከናውኗል፡፡ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የፀጥታ አጋር አካላት ጋር ሊከናውን የታቀደው የፀጥታ መረጃ ልውውጥ በታቀደው መሠረት ተከናውኗል የዕቅድ አፈፃፀሙም 100%ሆኗል፡፡ በእምነት ተቋማት መካከል የሚፈጠረውን አለመግባባቶችን በሰላም እንዲያልቁ የመምከር የማሳሰብ ፣የመደገፍና የመከታተል ተግባራት በእቅዳቸው መሠረት ተከናውነዋል፡፡ በአስተዳደሩ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎችና ማረሚያ ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎችን በየወሩ በመጎብኘት የታራሚዎቹን ችግር የማቃለል ሥራ የዕቅዱን 100% ተፈፅሟል፡፡ 
የተጠርጣሪዎች ታራሚዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ማክበርና ማስከበርን በተመለከተ የፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍሎች የመዝገብ አያያዛቸውን በመፈተሸ፤ በጊዜ ቀጠሮ አጠያየቅ ቃል አቀባበል በ48 ሰዓት ፍ/ቤት በማቅረብ ወዘተ ዙሪያ፣ በቁጥጥር ሥር የዋለ ተጠርጣሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ከህግና ከሀይማኖት አማካሪዎቻቸው የመገናኘት መብታቸው፣ መከበሩን የመከታተል ሥራዎች በስድስት ወራት 6 ጊዜ የዕቅዱን 100% ተከናውኗል፡፡ 18 ዓመት ያልሞላቸው የህግ ታራሚዎች ከሌሎች ታራሚዎች ተለይተው መያዛቸውን ከወላጆቻቸው ጋር ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ህፃናት ልዩ እንክብካቤ የማግኘት መብታቸው መከበሩን መከታተል ሥራ በ6 ወራቱ ዕቅድ መሠረት 100% ተከናውኗል፡፡
የህዝብና የመንግሥትን ጥቅም በመወከል በፍትሀብሔርና ወንጀል ጉዳዮች በፍርድ ቤት ክስ መስርቶ የመከላከል በህዝብና መንግሥት ላይ ለሚመሰረቱ ክሶች ምላሽ መስጠት፣ በተወሰኑ ውሣኔዎች ላይም የሰበርና ይግባኝ አቤቱታ ማቅረብ፣ ለመንግስትና ህዝብ የተወሰኑ መዝገቦችን የአፈፃፀም ክስ መስርቶ የመከታተል ተግባራት በዕቅዳቸው መሠረት ተፈፅመዋል፡፡ በአስተዳደሩ አስፈፃሚ እና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት ተዘጋጅተው ለአስተዳደሩ ም/ቤትና ካቢኔ የሚቀርቡ ከ10 በላይ ረቂቅ ህግች ህገመንግስቱን፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር እንዲሁም ከሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ጋር በማይቃረን መልኩ የተዘጋጁ በመሆናቸው በማረጋገጥ የህግ አስተያየት ይሰጥቷል፡፡
በግጭት መከላከልና አፈታት ረገድ በከተማና በገጠር እሉታዊ የግጭት መረጃዎችን በመሰብሰብና መተንተን፤ ፈጥኖ ምላሽ በመስጠት፣ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት በመቆጣጠር በህጋዊና ባህላዊ መንገድ በእርቅና በድርድር መፍታት፤ ግጭቶቹ ዳግም እንዳያገረሹ መከታተል የግጭት መንስኤዎችን መረጃ መያዝ ሥራዎች በእዳቸው መሰረት 100% ተከናውኗል፡፡
የሚሊሺያ ኃይሉን በማጠናከርና አቅሙን ለመገንባት በስድስት ወራት 690 የሚሊሺያ አባላትን ከህዳር 22 እስከ ታህሳስ 03 2007 ዓ.ም በ9 ካምፕ በማስገባት የወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅማቸውን ያጎለበተ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም በገጠር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርና ኮትሮባንድ ንግድ መካከል፣ የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን የመከላካል እንቅስቃሴ በገጠር የመደገፍና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የሚስጨብጥ መድረክ፤ በመፍጠር ገጠሩ ህብረተሰብን የመርዳት ተግባራት በስድስት ወራት ዕቅድ መሠረት ተከናውነዋል፡፡ 

በ2007 ዓ/ም ከ90 በላይ የትራፊክ አደጋ የተመዘገበ ሲሆን ከብር 700,00 /ሰባት መቶ ሺህ ብር/ በላይ በንብረት የደረሰ ጉዳት ተመዝግቧል፡፡ በወንጀል ምርመራ ረገድ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የምርመራ አፈፃፀምን ማሻሻል፤ የተከሳሾችና የምስክሮች አቀራረብ ብቃትን ማሳደግ፤ ለወንጀል ምርመራ ግብዓት የሚሆኑ ማስረጃዎችን አጠቃቀም ማሳደግ፣ የመረጃ አያያዝን ማሳደግ፤ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ የልማታዊ ዲሞክራሲዊ መንግሥት ፖሊሲዎችና ዓላማዎች በብቃት መፈፀም የሚችል ተጠቃሚነት ያለው በግልፅነትና በተጠያቂነት መርሆዎች ላይ ተመስርቶ ሀገርን ህዝብንና ዜጋን የሚያገልግል ጠንካራ ውጤታማ ሲቪል ሰርቪስ የመፍጠር ተልዕኮን ለማሳካት በስድስት ወራት ውስጥ በተደረገ እንቅስቃሴም፣
የቢሮው በየ2006 ዓ/ም የእቅድ አፈፃፀምን ከሠራዊት ግንባታና ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር አስተሳስሮ በመገምገም፣ ሂስና ግለሂስ በማካሄድ አመራሩንና ፈፃሚውን በደረጃ መለየት ተችሏል፡፡የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈፃጸም ምዘና ተካሄዷል፡፡
የቢሮውን የ2007 ዓ/ም ዕቅድ በማዘጋጀት ለፈፃሚዎችና ለባለድርሻ አካላት ለህዝብ እና ለድርጅት ክንፍ ኦረንቴሽን በመስጠት በቢሮ ደረጃ የተዘጋጀውን እቅድ በውጤት ተኮር አሰራር መሰረት ለሂደቶችና እስከ ፈፃሚድረስ እቅዱን በማወረድእና በመፈራረም ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት ተችሏል፡፡ በ8ቱ የለውጥ ስራ አመራር መሳሪያዎችና የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ደንብና መመሪያዎችን ወቅቱ ከሚፈልገው አገልግሎት አንፃር ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል በአዲስ የሚዘጋጁ የሚሻሻሉ አደረጃጀትና ሰነዶች በመለየትና ሰነዶችን በማጠናቀቅ ወደ ስራ ለመግባት ተችሏል፡፡ የተለያዩ የስልጠና ሰነዶችን፣ የማስፈፀሚያ ማንዋሎችና መመሪዎችን ወዘተ ማሻሻል እንደ አስፈላጊነቱ በአዲስ ማዘጋጀት፤ ተቋማት ከሰው ኃይል፣ ከአደረጃጀት ፤ ከግብዓት እና ከአሰራር አንፃር ያለባቸው ክፍተት በቢሮው በድጋፍ ክትትል ቲም የመለየት ስራ ተከናውኗል፡፡
በሀገር ደረጃ ተግባራዊ እየሆነ ያለውን የመልካም ልማታዊ አስተዳደር ጉዳይ በአስተዳደራችን በከተማእና በገጠርቀበሌዎችና በማዕከል ደረጃ ወደ 21,159. አባላትን በ2ኛው ዙር የመልካም ልማታዊ አስተዳደር የህዝብ ንቅናቄ ላይ በማሳተፍ አገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ህዝብን በማሳተፍ ችግሮችን በተደራጀ መልኩ የመለየት ስራ ተከናውኗል፡፡ በአስተዳደር ደረጃ አንድ የመልካም አስተዳደር እና የዕቅድ የኪራይ ሰብሳቢነትን ማድረቂያ ስትራቴጂ ሰነድ በከፍተኛ አመራሩ አፈፃፀሙ የሚገመገም የእቅድ ሰነዶች ተዘጋጅቷል፡፡
በ9ጠኙም የከተማ ቀበሌ፤ በ11 ቢሮዎችና በጽ/ቤት በስራቸው በሚገኙ የስነ ምግባር መኮንን ሁሉም ተቋማት የራሳቸውን የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጭ በመለየትና ማድረቂያ ስትራቴጂ ሰነድ አዘጋጅተው ለ1ለ5 እና በጋራ አፈፃፀሙን እንዲገመግሙ ምችችት ተደርጓል፡፡ 
በአስተዳደሩ ማነጅመንት ኢንስቲትዩት የስልጠና ፍላጎቶችን በማጥናት ቅደም ተከተል ሰጥቶ በማቀድ የመተግበር አፈጻጸም በታቀደው መሰረት ተከናውኗል፡፡ በሌላ በኩል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶችን የልማታችን ተሣታፈና ተጠቃሚ ለማድረግም በስድስት ወራት የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶችን ያሉበትን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚያስችል ክትትል በማድረግ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት የሚያስፈልጋቸውን የቁሳቁስ ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡
የአስተዳደሩ የሴቶች አመራር ፎረም ተመስርቷል ፤በገጠር ሥራ አጥ ወጣቶችን ለመለየት በተደረገው ዳሰሳ 853 ወንድ 183 ሴት በድምሩ 1036 ከ8ኛ ክፍል እስከ ዲግሪ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሥራ አጦች ተለይተዋል፡፡
ወጣቶችን በተለያዩ መስኮች በበጎ ፍቃድ ተግባራት በማሰማራት ከአደረጃጀቶችና ከሚመለከተው ሴክተሮች ጋር በቅንጅት በተሠራው ሥራ በዘጠኝ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዘርፎች 35,000 ወጣቶችን በማሳተፍ ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሥራ አከናውነዋል፡፡ የድጋፍና እንክብካቤ ሥራዎችንም በተመለከተ በበጀት ዓመቱ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚገባ 1310 አቅመ ደካማ ህፃናትን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በሚኒይስትሪሚንግ ዙሪያም ሴክተሮች የስርዓተ ጾታና የወጣቶች ጉዳይን በተሻሻለ መልኩ አካተው እንዲተገብሩ ለፕላንና ፕሮግራም ባለሞያዎች ለቀበሌ ሴቶችና ወጣቶች ማስተባበሪያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የእቅድ ዝግጅታቸውም ከስርዓተ ፆታ አንፃር የተቃኘ መሆኑን የሚያስችል መሆኑን ግምገማ ተካሂዷል፡፡ የግምገማ ግብረ መልስ በመድረክና በፅሁፍ ለሁሉም ሴክተሮች እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
በገጠር 4 አማራጭ ወጣት ማዕከላትን ለወጣቱ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ አፈፃፀሙም 80% ሆኗል፡፡ በከተማና በገጠር አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ወጣት ማዕከላትና የሴትና የወጣት አደረጃጀቶችን ነባራዊ ሁኔታ ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል አፈፃፀሙም 90% ሆኗል፡፡ ሴቶችና ወጣቶችን በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት እድል (እስኮላር ሺፕ) እንዲያገኙ ምችችት የማድረግ እቅድ 52% ተካናውኗል፡፡ በተጨማሪም ተጋላጭና ሴተኛ አዳሪ ለሆኑ ሴቶች የንግድ ክህሎትና ቁጠባ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ለተለያዩ በደል ለደረሰባቸው የህግ ድጋፍ መስጠት 70% የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ላጋጠማቸው ሴቶችና ወጣቶች ልዩ ልዩ ድጋፍ ማድረግ 50% የታቀደውን ተከናውኗል፡፡በት/ቤቶች እየተስፋፋ የመጣውን ለሱስ ተጋላጭነትና አደገኛ እፅ ተጋላጭነት ለመከላከል ለት/ቤቱ ማህበረሰብና ተማሪዎች የግዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የታቀፈውን 100% ተከናውኗል፡፡ወላጆቻቸውን ላጡና ለችግር ለተጋለጡ አካል ጉዳተኞች የህክምና ድጋፍ ማድረግ የእቅዱን 73% ተከናውኗል፡፡ ለ26 ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው መልሶ በማቀላቀል የማቋቋሚያ ድጋፍ ማድረግን የተመለከተ የታቀደውን 100%ተከናውኗል፡፡
በመጨረሻም አስተማማኝ የኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት በማስፈን ብቃትና በከፍተኛ ሥነ-ምግባር የታነፀ በ6ቱ ወራት የኮሙዩኒኬሽን ኃይል በማፍራትና ስትራቴጂያዊ አሰራር በመስጠት በመረጃ የበለፀገ ተሳታፊ ህዝብ ብሔራዊ መግባባት የሰፈነበት፣ በጎ ገፅታ ጎልቶ የወጣበትና የፈጣን ምላሽ አሠራር ሥርዓት ያዳበረ አስተዳደር የመገንባት ተልዕኮን ለማሳካት የአስተዳደሩ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በስድስት ወራት ባደረገው እንቅስቃሴ፣
በየሳምንቱ አቋም መግለጫና የአስተዳደሩን መልዕክት አዘጋጅቶ በድሬ ኤፍ ኤም ራዲዮ አማካኝነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ መሰረት 24 መልዕክቶችና 24 አቋም መግለጫ ተዘጋጅተው በድሬ ኤፍ ኤም ሬዲዮ አማካኝነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ በአስተዳደሩ የልማት ሥራዎች ዙሪያዎችና ውሳኔ ባገኙባቸው የህዝብ ጥያቄዎች 12 ፕሬስ ሪሊዞች ተዘጋጅተዋል፡፡
በአስተዳደሩ በሰላም ልማትና መልካም አስተዳደር አንዲሁም አስተዳደራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር 12ሺ ኮፒ ጋዜጣ ታትሞ ተሰራጭቷል፡፡ በአስተዳደሩ የሚከናወኑ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች መሠረት በማድረግ በየሩብ ዓመቱ መጽሔት ለማዘጋጀት በተያዘው እቅድ መሠረት የ2007 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የዳሰስና ለከተሞች ፎረም ልዩ መረጃ የምትሰጥ 1000 መጽሔት ታትሞ የተሰራጨ ሲሆን በተጨማሪ ይህን የግማሽ አመት የሥራ አፈፃፀም መሠረት ያደረገና የከተሞች ፎረም ያስገኘውን ፋይዳ የምትዳስስ መጽሔት አጠናቆ ለማሳተም በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
በግማሽ ዓመቱ 48 የሥምሪት ዜና ለማዘጋጀት ዕቅድ የተያዘ ቢሆንም በአስተዳደሩ የሚሠሩ የሰላም የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣና የተቋማትም የሚዲያ ፍላጎት ከፍተኛ እየሆነ በመሄዱ የተነሣ 144 ዜናዎች ተሰርተው ለህብረተሰቡ ተደራሽ አንዲሆን ተደርጓል፡፡
የአስተዳደሩን መልካም ዕሴትን ለማጎልበትና ድሬደዋ የፍቅር፣ የሰላም ከተማና ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ተከባብረውና ተቻችለው የመሠረቷት ከተማ በመሆኗ በሚከበሩት ሃይማኖታዊ ባዕላትን መሠረት በማድረግ

የአስተዳደሩን መልዕክት የያዘ መረጃ BULK SMS ለ76,120 ሞባይል ተጠቃሚዎች የኢድ -አልፈጥር ፣ የአዲስ ዓመት፣ የኢድ አል አዳና የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ተላልፏል፡፡ በተለያዩ የአስተዳደሩ የትኩረት አቅጣጫዎችና ሐገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ 24 የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ለማዘጋጀት በተያዘው ዕቅድ መሰረት የከተሞች ፎረም ፣የህዝብ ንቅናቄን በሚመለከት የመንግስት ሰራተኞች ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ የሚዘክር፣ የአስተዳደሩን የአራት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም የሚዳስስ ፣ የከተሞች ፎረም ቅድመ ዝግጅትን የሚመለከት፣በከተማ ኮማንድ ፓስት እንቅስቃሴ እና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ 24 የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ተዘጋጀተው በድሬ ቲቪ አማካኝነት ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
በየሣምንቱ አንድ መንግስታዊ የሬዲዮ ፕሮግራም ለማዘጋጀት በታቀደው መሠረት በሰንደቅ ዓላማ ቀን፣የከተሞች ፎረም የዝግጅት ምዕራፍና የየዕለቱ እንቅስቃሴ በሚመለከት፣ የከተማ ውበትና ጽዳትን፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ሥራ እንቅስቃሴን፣ የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን፣ የፆታ ጥቃትንና አካል ጉዳተኞችን በሚመለከቱ 24 የሬዲዮ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው በኤፍ ኤም ድሬ አማካኝነት በአየር ላይ ውሏል፡፡
በድረ-ገጽ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሶማልኛ እና በእንግሊዘኛ 480 ወቅታዊና የታቀዱ ዜናዎችን በድረ-ገጽ ለመጫን በተያዘው እቅድ መሠረት በተለይ በአስተዳደሩ ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳዳርላይ ያተኮሩ በአማርኛ 141 ፣ በኦሮምኛ 140፣በሶማልኛ 23፣በእንግሊዝኛ 23 በጠቅላላው 326 ወቅታዊና የታቀዱ ዜናዎች ተጭነዋል፡፡ የሰንደቅ ዓላማ፣ ቀንን ከተሞች ፎረም፣ ድሬ የቱሪዝም ማዕከል፣ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል የሚያንፀባርቁ 4 ስፖቶች ተዘጋጅተዋል፡፡ 6ኛው የከተሞች ፎረም ዝግጅት በተመለከተ የድሬደዋን መልካም እሴቶች እና የምስራቅ ኢትዮጵያ የኢንደስትሪና የአገልግሎት ማዕከል ለማድረግ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ለማስተዋዋቅ ሁለት ዶክመንተሪ ፊልሞች ተዘጋጅተው ከተለያዩ ክልል ከተሞች ለመጡ እንግዶች እንዲሠራጭ ተደርጓል፡፡
የሰንደቅ አላማ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን የከተማ አቀፍ ኢግዝብሽን፣ 6ተኛውን የከተሞች ፎረም፣ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ አቀባበል፣ የመጀመሪያው አገር አቀፍ የሴቶች ስፖርት ውድድርን እንዲሁም የገና ሁነትን በማስመልከት የመስኮት ኢግዚቭሽን ተካሂዷል፡፡ እንዲሁም የ6ኛ የከተሞች ፎረም በማስመልከት አስተዳደሩን ወክለው ወደዋናው የከተሞች ፎረም ውድድር የሚሣተፉ ሴክተር መ/ቤቶች እና ቀበሌዎችን ለማወዳደር በተዘጋጀው የከተማ አቀፍ ኤግዝቭሽን መስፈርትን መሠረት በማድረግ ለሁለት ቀን በምድር ባቡር አደባባይ የከተማ አቀፍ ኤግዝቭሽን የተካሄደ ሲሆን የአስተዳደሩ ነዋሪ በዝግጅቱ በንቃት የተሳተፈበትና ገንቢ አስተያየት የሰጠበት መድረክ የሆነና በዋናው ዝግጅቱም የሚሳተፉ ሴክተር መ/ቤቶችና ቀበሌዎች ተለይተው አስተዳደሩን በመወከል እንዲሳተፉ የተደረገና በዚህም የገፅታ ግንባታና ውጤታማ ሥራ ለማሥራት ተችሏል፡፡
አስተዳደራዊና አገር አቀፍ ጉዳዮችን የሚመለከቱ የተለያዩ የፅሁፍ ህትመት ውጤቶችንና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችን ሞኒተር ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ መሰረት አዲስ ዘመን፣ ኢትዮጵያን ሄራልድ፣ ራፖርተር፣ አዲስ አድማስ፣ ኢትዮ ቻናል፣ ሜዲካል፣ ካፒታል፣ ፎርቹን፣ አዲስ ጉዳይ ፣ወዘተ/ እና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችን /ቪኦኤ፣ ዶቼቬሌ፣ ዋልታ፣ ኦሮሚያ ቲቪ፣ ኤፍ ኤም ድሬ ቲቪ፣ ኢቲቪ ፣ BBC፣ ወዘተ/ሞኒተር በማድረግና የተተነተኑ ሞኒተሪንግ ውጤቶችን ለሚመለከታቸው አካላት ተደራሽ ተደርጓል፡፡ የህትመት እና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በወሩ ያተኮሩባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በመቃኘት 3 የአዝማሚያ ትንተና በማካሄድ ለሚመለከተው አካላት እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
በየሳምንቱ በወቅታዊ ጉዳዮችና አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው ዋና ዋና ጉዳይ ዙሪያ እንዲሁም በህዝቡ ውስጥ የተፈጠሩ አመለካከቶችን ለማወቅና ለቀጣይ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ 24 የህዝብ አስተያየቶችን ለማሰባሰብ በተያዘው እቅድ መሠረት 20 የህዝብ አስተያየቶችን በመሰብሰብ፣ በማደራጀትና በመተንተን ለሚመለከታቸው አካላት ተሰራጭቷል፡፡
በተመረጡ ዋና ዋና አስተዳደራዊ ክንውኖች እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዩችን መሠረት በማድረግ የተሠሩ ስራዎችን፡- በአገራችን ኢቦላን በመከላከል እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ፣የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን፣ የ6ተኛው የከተምች ፎረምን፣ የትራንስፖርት ስምሪትን ለማስተካከል የታፔላ መስመር መጀመርን፣ ምርጫ 2007 ዝግጅትን፣ የአስተዳደሩ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የአራት አመት የዕቅድ አፈፃፀም ማጠናቀቂያ መረጃዎችን ወዘተ ለፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ 6ኛው የከተሞች ፎረም በማስመልከት የአስተዳደሩን ነዋሪ በበዓሉ ላይ በጽዳት፣በፀጥታ መጠበቅ ፣ በእንግዳ አቀባበል ፣ በገጽታ ግንባታ፣ በጉብኝት ወዘተ በንቃት እንዲሳተፍ የህዝብ ንቅናቄ መወያያ ሠነድ በማዘጋጀት እና በማወያየት በሁሉም ቀበሌዎች የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች በመፍጠር በዓሉ የተሣካ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
የአስተዳደሩን የኢንፎርሜሸን ፍሰትና ቀጣይነት እንዲሁም አገልግሎቱም ተደራሽነት ከማሳደግ አኳያ የአስተዳደሩ የከተማ 9ኙም ቀበሌዎች እና ሴክተር መ/ቤቶች የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂካዊ መሪ ዕቅድ የወረደላቸው ሲሆን በየወሩ በሚደረገው የዘርፉ ፎረም አፈፃፀማቸውን የገመገመና መልካም ተሞክሮዎችን የማስፋት እንዲሁም የቀጣይ ተልዕኮችን አቅጣጫ በማስቀመጥ መረጃዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድርገ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡
በየሩብ ዓመቱ የመንግስት ወቅታዊ መረጃዎችና በአስተዳደሩ ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ ለህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ባሉ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች ተደራሽ ለማድረግና የህዝብ የመረጃ ማግኘት መብቱን ለማረጋገጥ በቢሮው አቅጣጫ እየተሰጠና አፈፃፀሙም ክትትል ተደርጐበታል፡፡
ሰትራቴጃያዊ አጋርነትን ከማሳደግ አንፃር መረጃዎችን በአስተዳደሩ ባሉ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች ተሻሽሎ በወጣው የት/ቤቶች ሚኒ ሚዲያ ማንዋል እና የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራምና መልዕክት ዝግጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና የተሰጠ እና ለሚኒ ሚዲያ አጀንዳ የሚሆኑ የተለያዩ የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ውጤቶች እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here