በከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ ሰላምን ለማስቀጠል በሚቻሉበት ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

0
839

ባለፉት ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ የተወሰኑ ቤቶች ላይም የቃጠሎ አደጋ ከመድረሱም በላይ ለሰው ህይወት አልፋል፡፡በከተማው ተከስቶ የነበረው ግጭት በፀጥታ ሀይሎችናበነዋሪ ህብረተሰብ ያለሰለሰ ርብርብአሁን ላይየተረጋጋ ሰላም ማስፈን ተችሏል፡፡

በከተማ አስተዳደሩም ተከስቶ በነበሩት ግጭቶችና አለመረጋጋትን አስመልክቶ በቀጣይ ሰላምን ለማስፈን ብሎም ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን በዚህም ውይይት ላይ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደረጃ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አህመድ ቱሳ የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አቶ መላኩ ፋንታ የአስተዳደሩ ከንቲባ ኢብራሂም ኡስማንና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ኡጋዞችና ኡለማዎች እንዲሁም ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄዶል፡፡

በውይይቱ ላይም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየት የተሰጡ ሲሆን በከተማው የስራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት፣ በኦሮሞና ሶማሌ መካከል ምንም አይነት ልዩነቶች እንደሌሉና አንድ ህዝብ በመሆናቸው ማንም እንደማይለያያቸው ተናግረው በአስተዳደሩ ጉዳይ ላይ የሁለቱ ክልል መንግስታት ብሎም የፌደራል መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በአስተዳደሩ ተከስቶ በነበረው ግጭት ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ለህግ መቅረብ እንደሚገባቸውም ነው ተሳታፊዎቹ የተናገሩት፡፡

የኦሮሚያና ሶማሌ ክልል መንግስታትም ሆነ ድርጅቶች አቋም ድሬዳዋ ሁሉም ብሄር ብረሰቦችና ህዝቦች ያለምንም ስጋት የሚኖሩባት ከተማ እንድትሆን ማስቻል በመሆኑ በከተማ አስተዳደሩ ኢንደስትሪ ፓርክን ጨምሮ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ስለሚገቡ ከፍተኛ የስራ እድልን እንደሚፈጥር የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገልፀው በቀጣይም የሚታዩትን ክፍተቶች ለማስካከል ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራም ነው የተናገሩት፡፡

የድሬዳዋ ሰላም እንዲረጋገጥ ሁሉም በትኩረት ከመስራት ባለፈም አሁን ላይ በሀገራችን ብሎም በከተማ አስተዳደሩ እየመጣ ያለውን ለውጥ ሊያደናቅፍ የሚችሉ ማንኛውም ጉዳዮችን በጥንቃቄና በንቃት በመከታተል ከመንግስት ጋር በመፍታት ለአስተዳደሩ ሰላም በጋራ መስራት እንደሚገባ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደረጃ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አህመድ ቱሳ ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ በሀገራችን የመጣውን ለወጥ በዋናነትና በባለቤትነት ማስቀጠል የሚገባው ህዝቡ እንደሆነና የሚያጋጩና ሰላም የሚነሱ ጉዳዮች ላይ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ፈትሾ ለችግሮቹ መፍትሄ በመስጠት ከተማዋ የንግድና የኢንደስትሪ ማዕከል እንደመሆኗ መጠን ሰላሟ የተረጋገጠ ለሁሉ ዜጎች ምቹ የሆነች ከተማ ማድረግ እንደሚገባ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አቶ መላኩ ፋንታ ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here