‹‹ሴቶች በሰላምና ዴሞክራሲ ግንባታ ያላቸውን ሚና ከወትሮው በበለጠ እንዲያጎለብቱ ››ጥሪ ቀረበ፡፡

0
781

በአስተዳደሩ የሴቶች የሰላም ኮንፈረንስና የጀግኒት የማህበረሰብ ንቅናቄ ፕሮግራም “ጀግኒት አለመች፣አቀደች ፣አሳካች” በሚል መሪ መልዕክት ከዛሬ ጀምሮ በይፋ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል፡፡

የአስተዳደሩ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከተለያዩ ዘርፍ ከተወጣጡ ሴት የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር “ሴቶች ዘረኝነትን በመጠየፍ ለሰላማች ግንባር ቀደም ሚናችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል የሴቶች ጀግኒት ፕሮግራም ማስጀመሪያ ፕሮግራም   የተጀመረ ሲሆን በሀገራችን ለ 13ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ፤ የ16ቱ ቀናት የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ የሚጀመርበት ፕሮግራም አክብረዋል፡፡

የሴቶች የሰላም ኮንፈረንስና የጀግኒት የማህበረሰብ ንቅናቄ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከኒትባና የንግድ ኢኑድስትሪና ኢንቨስትመንተት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብደላ አህመድ እንደተናገሩት ታሪክም ሆነ የማህበረሰብ ሳይንስ እንደሚያስረዳን ሴቶች በአለም ታሪክ ውስጥለተከናወኑታላላቅለውጦችናእድገቶችቀዳሚተሰላፊበመሆንከፍተኛሚናተጫውተዋል ብለዋል ፡፡

ምክትል ከኒትባው አክለውም ይህንን ዋጋ የተነፈገ የሴቶችን አበርክቶ በማጉላትና በሌሎች ተመን የሚወጣላቸው ዘርፎች ያላቸው ሚና፣ ተሳታፊነትና፣ ተጠቃሚነት እንዲሻሻል መንግስት ህገመንግስቱን ጨምሮ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ስትራተጂዎችን፣ መመሪያዎችንና አስፈጻሚ መዋቅሮችን እንዲጠናከሩ በማድረግ በሁሉም ዘርፍ የሴቶችን ሚናናተሳታፊነትለማሳደግናለማጠናከርእየተንቀሳቀሱእንደሚገኙ ገልፀዋል ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳር ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሐመድ በእንኳን ደህና መጣችው ንግግር የተቀናጀ ሰፊ የህብረተሰብን ቅናቄ በማድረግ በማህበረሰቡ ውስጥ ሴቶችን በተመለከተ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ኋላ ቀር አመለከከት መቀየርና “ሴቶች “ይችላሉ” የሚለውን አስተሳሰብ ማምጣት ይኖርብናል በማለት በሁሉም ዘርፍ የተሻለ አበርክቶ ያላቸውን ሴቶችና የሴት ቡድኖች ከድሬዳዋ አስተዳደር ጀምሮ እስከ ልማት ቡድን ድረስ በመለየት ለስራዎቻቸው እውቅና መስጠት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም ሰላም ለአስተዳደራችን ብሎም ለሀገራችን ብልፅግና እና ለሁሉም ዜጎች ደህንነት ከምንም በላይ አስፈላጊ በመሆኑ ሴቶች በሰላምና ዴሞክራሲ ግንባታ ያላቸውን ሚና ከወትሮው በበለጠ እንዲያጎለብቱም ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በስነ-ስርአቱ ላይ የተሳተፉ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት በሃገራችን የተጀመረው ሴቶችን ወደ አመራርነት መምጣታቸው እንዳስደሰታቸው በመግለፅ በቀጠይ ጊዚያቸውም እራሳቸውን በሚፈለገው ደረጃ በማብቃት የተጀመረውን ለውጥ በተሰማሩበት የስራ መስክ እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል ፡፡

በስነ-ስርዕቱም የአስተዳደሩ ምክትል ከኒትባ አቶ አብደላ አህመድ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክት ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አብዱልሰላም መሀመድ፣ የካቢኔ አባላት፣ የሐይማኖት አባቶች ፣የሐገር ሽማግሌዎች፤ ኡጋዞችና አባገዳዎች እንዲሁም የአስተዳሩ ሴቶችና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here