ሰሞኑን በድሬዳዋ የተከሰተው ግጭት ከትላንትና ማታ ጀምሮ ሰላም መሆኑ ተገለፀ

0
619

በድሬዳዋ አስተዳደር በአንዳንድ አካባቢዎች የነበሩ ግጭቶች ከትላንትና ማታ ጀምሮ ሰላም መሆኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ገለፁ::

ኃላፊው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩ በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩትን ግጭቶችና ሁከቶች በፀጥታ ሀይሎች የተቀናጀና የጣምራ ስራ ሰላማዊ ሁኔታ መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ የድሬዳዋ ሰላም ለማስጠበቅ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ከህብረተሰቡ ጋር ስለ ሰላምና ሀገራዊ ግንባታ ዙሪያ ለመወያየት አቅጣጫ መቀመጡን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም የህግ የበላይነትና ለማረጋገጥ ከዚህ ጋር ተያይዞ ያሉትን ችግሮችን የመፍታት ስራ ህጋዊ ሂደቶችን ጠብቆ የማረጋገጡ ስራም እንደሚሰራ በመግለፅ በተጠናከረ መልኩ የአካባቢ ሰላም ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ ጋር በመሆን ያሉትን ችግሮች ቀድሞ የመቆጣጠር አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here