ዩኒቨርሲቲዎች በሀገር ሰላምና አንድነት የጎላ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ፡፡

0
705

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ግዜ ወዲ የተከሰተው ግጭትና ሁከት ድሬደዋንም በተወሰኑ አካባቢዎች የንብረትና የህይወት ማለፍ ተጎጂ አድርጓታል በዚህም እንደ ሀገር የሰላም ኮንፍረንስ እየተካሂደ ይገኛል ፡፡በዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካኤል በሚመሩት ቡድን ለአንድ ሳምንት ያክል ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በትላንትናው እለትም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ እንዲሆን በዩኒቨርሲቲው እና ለከተማው ማህበረሰብ የሰላም ኮንፈረንስ ውይይት የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል፡፡

የሰላም ኮንፍረንሱን ውይይት የመሩት የአአስተዳደሩ ከንቲባ ኢብራሂም ኡሱማን እንደተናገሩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአስተዳደሩ በተወሰኑ ቦታዎች እየተከሰተ ያሉት ግጭትና ሁከት መልኩን እየቀያየረ የድሬደዋን ሰላም ሲያሳጣት ቆይቷል፡፡ይህም በመሆኑ የድሬደዋን ሰላም ለማስጠበቅ ሁሉም አካላት ሚናውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ፡፡

በውይይት መድረኩም የዩኒቨርስቲው የ100 ቀናት የሪፎርም እቅድ በዩኒቨርስቲው ፕሪዘዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በቀረበው እቅድ ውስጥ ቢካተት ያሉትን በተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን የመምህራን ቤት ችግር ፣በዩኒቨርስቲው የግብአት እጥረት ፣የአካል ጉዳተኞች በዩኒቨርስቲው በትምህርት አሰጣጡ ያሉ ክፍተቶችን አንስተዋል፡፡

በተነሱት ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የዩኒቨርስቲው ፕሪዘዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ዩኒቨርስቲው የአካል ጉዳተኞችን ችግር ለመፍታት ከማህበሩ ጋር በቅርበት በመስራት የተነሱትን ችግሮች እንደሚፈታ በመግለፅ ከተሳታፊዎች የተነሱትን ጥያቂዎች በእቅዱ በማካተት ለእቅዱ ተፈፃሚነት ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር አብረው እንደሚሱም ገልፀዋል፡፡

በውይይት መድረኩም የዩኒቨርሲቲውን ሰላም ማረጋገጥ የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ ማለት ነው፣ የከተማውን ሰላም ማረጋገጥ የዩኒቨርሲቲውን ሰላም ማረጋገጥ ስለሆነ የአስተዳደሩና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ያሉት የምድር ባቡር ኮርፕሬሽን ስራአስኪያጅ ዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ለእቅዱ መሳካት የዩኒቨርሲቲውና የአስተዳደሩ ማህበረሰብ በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለወዋል   ፡፡

አስተዳደራዊ ጥያቄዎችን የመለሱት የአስተዳደሩ ከንቲባ ኢብራሂም ኡሱማን እንደተናገሩት የመምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ባሉት የቤት ልማት ፕሮጀክቶች ለመፍታት እየተኬደበት እንደሆነ በመግለፅ በቀጣይ ጊዜያት ለሚኖረው የመማር ማስተማር ሂደት ሁሉም የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀረበው የ100 ቀን የሪፎርም እቅድ ለማሳካት የድርሻቸውን እንደሚወጡ በመግለፅ በቀጣይ በመማር ማስተማሩ ሂደት የተሳካ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ቃል በመግባት አረጋግጠዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here