ብዝሃነት፣ መቻቻልና እርቅ ለአገራዊ አንድነት ግንባታ

0
683

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ ቋንቋ የሚነገርባት፤ በዛው ልክ ደግሞ የበርካታ ብሄሮች የጋራ መኖሪያ ናት፡፡ ከዚህም የተነሳ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አጀንዳዎችን ስናስብ ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ ሊሆን ይገባል፡፡ ህብረ-ብሄራዊነታችንን እና ብዝሀነታችንን ማነም ሊዘነጋው አይገባም፡፡ ይህን ያላገናዘበ እና ልዩነቶችን ያላስተናገደ የትኛውም አጀንዳ ሀገራዊ መግባባትን ሊያመጣ፤ አንድነትን ሊያጠናክር ከዚያም አልፎ  ስኬታማ ሊሆን አይችልም፡፡

ወደ አስተዳደራችን ተጨባጭ እና ነባራዊ ሁኔታ ስንመጣ ደግሞ መጠናቸው ይለያይ እንጂ በርካታ ብሄሮች በጋራ የሚኖሩባት ስለሆነች ያለውን ከመቁጠር የሌሉትን መቁጠሩ ይቀላል፡፡ ለዚህም ነው ምሁራን ትንሿ ኢትዮጵያ በማለት በቁልምጫ ስሟ የሚጠሯት፡፡ ስለሆነም ይህን ያላገናዘበ እና ልዩነቶችን ያላስተናገደ የትኛውም የአስተዳደሩ አጀንዳ የጋራ መግባባትን ሊያመጣ፤ አንድነትን ሊያጠናክር ብሎም ስኬታማ ሊሆን አይችልም፡፡

በሌላ በኩል የመተሳሰብን እና የመቻቻልን አስፈላጊነት በእጅጉ የሚያጎላው ብዝሀነታችን ነው፡፡ ልነቶቻችንን በማራገብ አንድነታችንን ሊፈታተኑ የሚፈልጉ ኃይሎች ዕድል እንዳያገኙ እና ወደብተና ብሎም ወደ ዕልቂት እንዳናመራ በብዝሀነታችን ልክ ልንተሳሰብ እና ልንቻቻል ይገባል፡፡ ከብዝሀነታችን የተነሳ የሚፈጠሩ ልዩነቶች በጥንቃቄ ከተያዙ ለአንድነታችን መጠናከር ግብዐት ናቸው እንጂ የሚለያዩን አይደሉም፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገራችን  አስደማሚ  ውጤቶች የተመዘገቡበት የለውጥ ጉዞ ጀምራለች፡፡ የለውጥ ጉዞው  ህገ-መንግስታዊ  አጀንዳዎችን ስለያዘ በፍቅር እና በይቅርታ  የመደመርን ብሎም አንድ የመሆንን ዓላማ ያነገበ ነው፡፡ በዚህች የጋራችን እና ለሁላችን መተኪያ  የሌላት ሀገር ውስጥ በጋራ ስንኖር በማወቅም ባለማወቅም አንዳችን ሌሎቻችንን አሳዝነን ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህም ሳቢያ በመካከላችን ቂም በቀል፣ ጥላቻ እና ቆርሾ ተፈጥሯል፡፡

ስለዚህ አንድነታችን እንዳይጠናከር ብሎም ወደ ዕልቂት እና ብተና እንድናመራ የሚፈልጉ ኃይሎች ይህን ክፍተት እንዳይጠቀሙ ያለፉ የተሳሳቱ ግንኙነቶቻችንን በፍቅር እና በይቅርታ ተደምረን አንድነታችንን በማጠናከር  ልናስተካክላቸው ይገባል፡፡

ይህንን  አጓጊ እና አሰገራሚ ውጤቶች እየተመዘገበበት ያለውን ለውጥ ሊያደናቅፉ የሚችሉና ሁኔታዎችን በሚገባ ለይቶ ዙሪያ መለስ ርብርብ ማድረግ ይገባል፡፡  በተለይ በአሁን ወቅት የላቀ ትኩረት የተሰጠውን የለውጡ አንድ አካል የሆነውን የአገራዊ አንድነት ግንባታ ሂደት በተፈለገው ፍጥነት እንዳይሄድ እያደረጉ የሚገኙ ክስተቶች  እና የክስተቶቹ ምክኒያቶች እንደ ችግር   በሚፈቱበት አግባብ ላይ አስተዳደሩ እና ነዋሪው ሊመክሩ ይገባል፡፡

አንድ ላይ ስናጨበጭብ እንደመጣለን፡፡ ስንደመር አንደነታችን ከምን  ጊዜውም በላይ በማይቀለበስበት ደረጃ ይጠናከራል፡፡ ብዝሀነትን ያስተናገደ በዚህ መሠረት ላይ የተገነባ ጠንካራ  ሀገራዊ አንድነት እና በመተሳሰብ፣በመቻቻል፣በፍቅር ብሎም በይቅርታ ይብልጥ እየተጠናከረ የሚሄድ አንድነት ለጋራ ራዕያችን ዕውን መሆን በእጅጉ ያስፍልገናል፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

                                                     ድሬዳዋ

                                                       28/03/2011ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here