መብትን ማስከበር የሚቻለው በህጋዊ መንገድ ብቻ ነው

0
640

በየትኛውም ሀገር እና በየትኛውም የመንግስት ሥርዓት ከራስ ወዳድነት ስሜት የሚመነጩ የግለኝነት፣ ጠባብነት እና ትምክህት አመለካከቶች እስካሉ ድረስ የጥቅም ግጭቶች እና የመብት ጥሰቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በመሠረቱ በእንደዚህ ያለ ስሜት የተለከፉ እና በአመለካከቶቹ የተጠመዱ ዜጎች በህግ የበላይንት አያምኑም፡፡ ከዚህም የተነሳ ከማንም ጋር በሠላም ሊኖሩ ስለማይችሉ  ከቤተሰብ እስከ ሀገር የማፍረስ እንጂ ሌላ ሚና ሊኖራቸው አይችልም፡፡

       ስለሆነም እንደዚህ ያሉ አደገኛ እና የሀገርን ህልውና የሚፈታተኑ አመለካከቶች ከነተግባራቸው ከመታየት አልፈው በሥርዓቱ ላይ ጥላ ማጥላት ሲጀምሩ መንግስት አሁን እያደረገ እንዳለው የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና ማንም ከህግ በላይ ያለመሆኑን በተግባር ማሳየት በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡

       በአሁኑ ወቅት መንግስት ራሱ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ብሎም የማክብር ትልቅ ኃላፊነት ስላለበት በተረጋጋ እና ብስለት በተሞላበት ስልት የህግ የበላይንትን በህጋዊ መንገድ ብቻ ለማረጋገጥ እየተከተለ ያለው አቅጠጫ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡

       ብቸኛ አማራጭ ነው የምንልበት ዋናው መነሻ ምክኒያት የዜጎችን መብቶች ማስከበርም ሆነ ሀገርን ከመበታተን ማትረፍ የሚቻለው በዚህ መንገድ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ አለበለዚያ ግን ያለፈን ስህተት በመድገም  በሀገር እና በወገን ላይ ተጨማሪ የመበታተን  አደጋ ስጋቱ መልሶ እንዲያንዣብብ ማድረግ ይሆናል፡፡

       እንደ ህዝብም ይህን ተጨባጭ እውነታ በቅጡ በመረዳት  በሚያስፈልገው ሁሉ ከመንግስት ጎን ልንቆም ይገባል፡፡ እኛም መብቶቻችንን በህጋዊ መንገድ ብቻ በማስከበር የተጀመረው በህጋዊ መንገድ ብቻ የህግ የበላይንትን የማረጋገጡ ሥራ ውጤታማ እንዲሆን የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል፡፡

       የወቅቱ አንገብጋቢ አጀንዳችን በህጋዊ መንግድ እና ህጋዊ መንግድ ብቻ የህግ የበላይንትን በማረጋገጥ ሠላምን የማስፈን እና እያንዣበበ ያለውን የመለያየት የስጋት ደመና ማስወገድ ነው፡፡ ሀገር እና ወገንን ወዳድ ዜጋ ሁሉ በግጭት፣ በሁከት እና በህገ ወጥንት የባከኑ ዓመቶቻችን ሊቆጨው ይገባል፡፡

       ስለዚህ በዚህ ትልቅ ፋይዳ ባለው በዚህ  ሀገራዊ አጀንዳ ሁላችንም የጋራ መግባባት ፈጥረን በህጋዊ መንገድ ብቻ የህግ የበላይንት እንዲረጋገጥ፤ የበኩላችንን አስትዋፅኦ በማድረግ ልንረባረብ ይገባል፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

                                                     ድሬዳዋ

                                                       20/03/2011ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here