መብቶቻችንን በህጋዊ እና ህጋዊ መንገድ ብቻ ልንጠቀም ይገባል

0
579

ሥርዓቶች ቢፈራረቁም አፈናውና ጭቆናው ባንገፈገፈው የብሄረሰቦች ስብስብ የተራዘመና ብዙ መስዋዕትነት በጠየቀ መራራ ትግል ዕውን የሆነው ሕገ-መንግስታችን በርካታ መብቶችን አጎናጽፎናል፡፡ እነዚህ መብቶቻችን በማያሻማ መልኩ በሁለት መሠረታዊ የመብት ዓይነቶች በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህ የመብቶቻችን ዓይነቶች ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመባል ይታወቃሉ፡፡

ሰብዓዊ መብቶቻችን ሰው ሆነን በመፈጠራችን ብቻ የምንጎናጸፋቸውና በማንም ፍቃደኝነት የማይሰጡን እንዲሁም የማይወሰዱብን መብቶቻችን እንደሆኑ ህገ-መንግስታችን ያሰረዳል፡፡ ይህን የህገ-መንግስቱን እሳቤ ራሳችን በሚገባ አንብበን፤ እንዲሁም ከህግ ባለሙያዎችን በመጠየቅ ጥርት ያለ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በአጠቃቀመቀችን ሂደት በሚፈጠር ስህተት ችግር ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡

ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ተብለው በህገ መንግስቱ ላይ በዝርዝር የተቀመጡት መብቶቻችን ደግሞ ለፖለቲካ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዙ በመሆናቸው በመንግስት ሲፈቀድልን የምንጠቀምባቸው መብቶቻችን ናቸው፡፡ ስለዚህ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን መንግስት ሀገር የማስተዳደር ኃላፊነት ስላለበት በመንግሰት ፈቃደኝነት ሲያስፈልግ በህጋዊ መንገድ ብቻ የሚሰጡና አላስፈላጊ ሆነው ሲገኙ ደግሞ  በህጋዊ መንገድ ብቻ የሚሰዱ ናቸው፡፡

ሰብዓዊም ሆኑ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችንን መጠቀም የምንችለው አነዚህን ከህልውናችን ጋር በእጅጉ የሚቆራኙ መብቶቻችንን ያጎናጸፈንን ህገ-መንግስት ስናከብር ብቻ ነው፡፡ ምክኒያቱም ህገ-መንግስቱ የሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ሁሉ የበላይ እንደሆነ ህገ-መንግሰቱ ራሱ ስለሚደነግግ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ህገ-መንግስቱ ሁሉም ዜጎች በህግ ፊት እኩል እንደሆኑ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

ስለዚህ የትኞቹንም መብቶቻችንን በህገ-ወጥ መንገድ መጠቀም ስንጀምር ህገ-መንግስቱ በራሱ መብቶቻችንን በህጋዊ መንግድ ይወስድብናል ማለት ነው፡፡ መንግስትም ህገ-መንግስቱ በሚሰጠው ሥልጣንና መብት ተጠቅሞ መብቶቻችንን  በህጋዊ መንገድ ይወስድብናል፡፡ መንግስት ይህን የሚያደርገው የሌሎችን ዜጎችን መብቶች የማስጠበቅ ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት ስላለበትም ጭምር ነው፡፡ ይኼ ከመብቶች ጥሰት ጋር በፍጹም የሚገናኝ አይደለም፡፡ ምክኒያቱም ህገ-መንግስቱ የፈቀደው ህጋዊ መንገድ በመሆኑ ነው፡፡

ስለሆነም የትኞቹንም መብቶቻችንን በህጋዊ መንገድ እና በህጋዊ መንገድ ብቻ በመጠቀም ለተያያዝነው የለውጥ ጉዞ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የራሳችንን አስትዋጽዖ ልናበረክት ይገባል፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

                                                     ድሬዳዋ

                                                       07/03/2011ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here