የ2011 ዓ.ም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች ቅበላ ከጥቅምት 15-18 እንደሚሆን ተገለጸ፡፡

0
535

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ሲቀበል ከቤተሰብ የተረከበውን አደራ በሙሉ ኃላፊነት ለመወጣት ከአስተዳደሩና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን እንደሚሰራ ዶ/ር ያሬድ ማሞ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስታውቀዋል፡፡

         የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ኡጋዞች፣ አባገዳዎች እንዲሁም የተለያዩ የባለድርሻ አካላት በታደሙበት የውይይት መድረክ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማንን ጨምሮ ከሲቲ ዞን አስተዳደርና ከመርመርሳ ጉዳዩይመለከተናል ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ስለ አካባቢው ሰላም ውይይት አድርገዋል፡፡

       በውይይቱም ላይ ድሬዳዋ ከተማ የፍቅር የአብሮነትና የመቻቻል ከተማ እንደመሆኗ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የተለያየ ሃይማኖት፣ ባህልና የአኗኗር ስርዓት ያላቸውን ወጣቶች በአንድ ላይ ለመኖር ሲመጡ ምን አይነት አቀባበል መደረግ እንደሚገባውና አሁን ያለውን የክልሉን ሰላም ለማስቀጠል ምን መደረግ እንዳለበት ውይይት ተደርጓል፡፡

       በውይይት መድረኩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ሁልጊዜ ችግሮች ሲፈጠሩ ብቻ የሀይማኖት አባቶችንና የሀገር ሽማግሌዎችን መሰብሰብ እንደ አማራጭ የሚታይ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ችግሮች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ግጭትን ለመከላከል፣ መልካም ስነ ምግባርን ለመገንባት፣ከምንም በላይ ደግሞ ለቀጣይ ስራችን ምክርና ድጋፍ ለማግኘት የእናንተ ሚና የማይተካና አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን የውይይት መድረክ አስቀድመን እንድናዘጋጅ አድርጎናል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ያሬድ ማሞ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው የአዲስ ተማሪዎች አቀባበል እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪም ሆነ እንደ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትኩረት የሚሰጠውና የሚያሳስበን ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

         ውይይቱን ማካሄድ ያስፈለገበት ዋንኛ አላማም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አስተዳደር የተከሰቱ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ላይ አስቀድሞ በመነጋገር ለማስተካከል እንዲደረግ ነው፡፡ ባሳለፍነው አመት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በነበረው ግጭት ሳቢያ የተለያዩ ወጣቶች ከነቤተሰቦቻቸው ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉበት፣ በነበረው አለመረጋጋት ለእስር የተዳረጉና የተለያዩ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ የነበሩ ተማሪ ወጣቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ይህንን የስነ ልቦና ቀውስ ተቋቁመው ወደ ተረጋጋ የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ እንዲገቡ ለማስቻል ዩኒቨርሲቲው በሚያደርገው እንቅስቃሴ ባልተናነሰመልኩ የድሬዳዋ ማህበረሰብም ጥሩ ፊት ከማሣየት ጀምሮ በአስተዳደሩ የሚሰጡ ማንኛውንም አገልግሎቶች ሲሰጡ ፍትሃዊ ና ቤተሰባዊ በሆነ መልኩ መሆን እንደሚገባው ከአደራ ጭምር አሣስበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲ ደሴት አይደለም!ብቻውን ምንም ሊሰራ አይችልም ያሉት ዶ/ር ያሬድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ በማድረግ ከቤተሰብ በእምነት የተረከብነውን አደራ ለመወጣት የሚመጥንዝግጅት በማድረግ ተማሪዎችን መቀበል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

           ከመድረኩ ተሳታፊዎች በተሰጠውም አስተያየት ተማሪዎች በተለያዩ ሱሶች በመጠመድ የመጡበትን አላማ እንዳይስቱ መምህራን ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን እንደ አባት በመምከር ስነ ምግባራቸውን ከማስተካከል አኳያ ትልቁን ሚና እንዲወጡ ማስቻል ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ያሉ መጠጥ ቤቶችና ሺሻ ቤቶች እንዲዘጉ ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በታሪፍ መሰረት እንዲሰሩ፣ ነባር ተማሪዎችና አዲስ ገቢ ተማሪዎች የጋራ የምክክር መድረክ እንዲኖራቸው በርካታ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ክቡር ከንቲባው ማጠቃለያ ሃሳብ ሰጥተውባቸዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here